ፈልግ

በሞናኮ የሚትገኘው ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮን በደስታ እየተጠባበቀች ትገኛለች በሞናኮ የሚትገኘው ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮን በደስታ እየተጠባበቀች ትገኛለች  

በሞናኮ የሚትገኘው ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮን በደስታ እየተጠባበቀች ትገኛለች

በሞናኮ የሚገኘው የአካባቢው ቤተክርስቲያን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን ሐዋርያዊ ጉብኝት በደስታ እና በጉጉት እየተጠባበቀች ትገኛለች፣ የሲቪል እና የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት የጳጳሱን ጉብኝት ታሪካዊ ባህሪ በማጉላት ልዩ ዝግጅት ለማዘጋጀት አቅደዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በሞናኮ የሚገኙ የክልል እና የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት በሞናኮ በሮክ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሉዓላዊ ጳጳስ የመቀበል ተስፋ በማሳየታቸው ተደስተዋል። ረቡዕ የካቲት 17/2018 ዓ.ም በወጡ ሁለት የፕሬስ መግለጫዎች፣ የልዑሉ ቤተ መንግሥት እና የሞናኮ ሊቀ ጳጳስ በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽሕፈት ቤት እኩለ ቀን ላይ የወጣውን መረጃ አረጋግጠዋል፡- ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ቅዳሜ፣ መጋቢት 19/2018  የሆሳህና በዓል ዋዜማ ወደ ሌ ሮቸር፣ “ዘ ሮክ” ጉዞ ያደርጋሉ።

ልዑል አልበርት 2ኛ በጥር 09/2018 ዓ.ም ወደ ቫቲካን ከባለቤታቸው ጋር መጥተው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጋር በተገናኙበት ወቅት ቅዱስ አባታችን ሞናኮን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበው እንደ ነበረ ይታወሳል።

“የልዕልት ቤተሰብ እና ርዕዮተ ዓለሙ ከጴጥሮስ ተተኪዎች ጋር ያለውን የዘመናት ትስስር እናውቃለን” ሲሉ የሞናኮ ሊቀ ጳጳሳት የተናገሩ ሲሆን የካቶሊክ እምነት የመንግሥት ሃይማኖት የሆነበት ሥፍራ እንደ ሆነም አክለው በመግለጫቸው ተናግረዋል። የሞኔጋስክ ቤተክርስቲያን ሁለቱ ሉዓላዊ መንግሥታት የተጋሩትን ቃል ኪዳን አስታውሳለች፤ ከእነዚህም መካከል “ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለሰው ልጅ ሕይወት አክብሮት ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ፤ ለኢኮሎጂ እና ‘የጋራ ቤታችን’ ጥበቃ፤ እንዲሁም ለስፖርት እና የሰው ልጅን የሚወክል የጋራ  ፍቅር” ይገኙበታል።

በልዑል በሚመራ አገር እና በቅድስት መንበር መካከል ለዘመናት የዘለቀ ትብብር

ጉብኝቱ እ.አ.አ ከ1297 ዓ.ም ጀምሮ ሞናኮን የገዛው የግሪማልዲ ሥርወ መንግሥት ከጴጥሮስ ተተኪዎች ጋር የሚያቆራኙት ቀጣይነት ያለው፣ ለዘመናት የዘለቀ ትስስር አካል ነው። በተጨማሪም የልዑሉ ቤተ መንግሥት የፕሬስ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው በዓለም ላይ በሁለቱ ትንንሽ ግዛቶች መካከል “ለረጅም ጊዜ የቆየ እና እምነት የሚጣልበት” የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

እ.አ.አ በሐምሌ 2021 የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፒትሮ ፓሮሊን በቅድስት መንበር እና በዋናው መንበር መካከል የተፈረመውን 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለማክበር በሞናኮ የሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፣ ይህም የሞናኮ ሀገረ ስብከትን ወደ የሊቀ ጳጳስ መቀመጫ ቤተ ክርስቲያን ክብር ከፍ ያደርገዋል።

ይሁን እንጂ፣ በሁለቱ ሉዓላዊ ትናንሽ ግዛቶች መካከል ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መመስረት የተጀመረው እ.አ.አ በ1887 ዓ.ም ሲሆን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 13ኛ፣ በላቲን ቋንቋ "Quemadmodum sollicitus Pastor" (እንደ አሳቢ እረኛ) በተሰኘ አርዕስት ተፍርሞ ይፋ የሆነው ሰንድ የሞናኮ ሀገረ ስብከትን በቀጥታ በቅድስት መንበር ስር እንዲተዳደር ወስነው ነበር። እ.ኤ.አ. በ2027 ዓ.ም፣ ሊቀ ጳጳሳት መቀመጫ ሆና የተሰየመችበትን 140 ዓመታትን የታሪክ ዘመን፣ እንዲሁም በሞናኮ ሮክ ተብሎ በሚጠራበት ሥፍራ ላይ የመጀመሪያው ቁምስና የተመሰረተበትን 780ኛ ዓመት ክብረ በዓል ያከብራሉ፣ ይህም እ.አ.አ በታህሳስ 6 ቀን 1247 በሊቀ ጳጳሳት ኢኖሰንት አራተኛ በላቲን ቋንቋ " Pro puritate" (ለንጽህና ሲባል) በተሰኘው ይፋዊ ሰንድ በኩል የተፈቀደ ነው። እነዚህ ሁለት ቁልፍ የዓመታዊ በዓላት የሊዮ 14ኛ ታሪካዊ ጉብኝት በፊት የተከሰቱ ክንውኖች ናቸው።  

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ የሞንጋስክ ሕይወት ማዕከላዊ አካል

የሞናኮ ርዕሰ መስተዳድር የካቶሊክ እምነት እንደ መንግሥታዊ ሃይማኖት ከያዙት ጥቅት የአውሮፓ አገሮች አንዷ ናት። እ.አ.አ በ1962ቱ ሕገ መንግሥት ከ38,000 በላይ ለሆኑ ሕዝቦቿ የአምልኮ ነፃነት የተረጋገጠ ቢሆንም፣ የአካባቢው ቤተክርስቲያን “በሞንጋስክ ሕይወት ውስጥ ማዕከላዊ ተቋም ሆና በብዙ መንገዶች ሕያው ሆና ትቀጥላለች፣ ብዙውን ጊዜ ለሕዝብ የማይታወቅ” ሲሉ ሊቀ ጳጳሱ አረጋግጧል።

በመጪው የቅዱስ አባታችን ጉብኝት የሚነሱት ተስፋዎች ሁሉ የበለጠ ይሆናሉ። ከጉብኝቱ ታሪካዊ ጠቀሜታ ባሻገር፣ የሊቀ ጳጳሱ መምጣት “በውይይት፣ በሰላም እና በጋራ ኃላፊነት መንፈስ ውስጥ ኃይለኛ የተስፋ ምልክት” ይሆናል ሲል የልዑሉ ቤተ መንግሥት አፅንዖት ሰጥቶ ይናገራል።  የሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ሁለተኛ ሐዋርያዊ ጉዞ ዝርዝር ፕሮግራም በቅርቡ ይፋ ይደረጋል።

27 Feb 2026, 14:46