ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በማዳጋስካር የአውሎ ነፋስ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት አደረጉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በማዳጋስካር የአውሎ ነፋስ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት አደረጉ  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በማዳጋስካር የአውሎ ነፋስ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት አደረጉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በየካቲት 08/2018 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በማዳጋስካር የተከሰተውን ተከታታይ አውሎ ነፋሶች ተጽዕኖ ተከትሎ ወደ 16,000 የሚጠጉ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላችሁን ገልጸው፣ በዚህ ምክንያት እየተሰቃዩ ለሚገኙ ሰዎች ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁለት አውሎ ነፋሶች ተጽዕኖ ለሚሰቃዩት የማዳጋስካር ሰዎች ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል። “ለተጎጂዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ እጸልያለሁ” ብለዋል።

በደቡብ ምዕራብ የህንድ ውቅያኖስ የተከሰተው የአውሎ ንፋስ በዚህ አመት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ማዳጋስካር ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ እና ጌዛኒ እና ፋይቲያ በደረሱት አውሎ ነፋሶች ምክንያት ዓለም አቀፍ እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

ጌዛኒ እ.አ.አ የካቲት 10 ቀን በአውሎ ንፋስ ከፍተኛ ውድመት ደርሶ ነበር፣ ይህም ወደ 270,000 የሚጠጉ ሰዎችን ነክቷል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችንም አፈናቅሏል። የአገሪቷ ባለስልጣናት ቢያንስ 40 ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት አድርገዋል። ከተባበሩት መንግስታት እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን የአገሪቱ ሀብቶች ለፈልጎ ማዳን፣ ለተፈናቀሉ ሰዎች ማቋቋሚያ፣ ለመጠለያ እና ለምግብ እርዳታ እንዲውል ተወስነዋል።

የጨረቃ አዲስ ዓመት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በምሥራቅ እስያ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የጨረቃ አዲስ ዓመትን ለማክበር እንዴት እየተዘጋጁ እንደሆነም አስተውለዋል። “ይህ አስደሳች በዓል” “የበለጠ ጠንካራ የቤተሰብ ግንኙነቶችን እና ጓደኝነትን ያበረታታል፤ ለቤተሰቦች እና ለኅብረተሰቡ ሰላምን ያመጣል፤ እናም ለወደፊቱ አብረን የምንመለከትበት፣ ለሁሉም ሕዝቦች ሰላምና ብልጽግናን የምንገነባበት አጋጣሚ ይሁን” የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የጨረቃ አዲስ ዓመት እ.አ.አ በየካቲት 17 ሲከበር፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለሁሉም ሰው የእግዚአብሔርን በረከት ከተመኙ በኋላ መልካም ምኞታቸውን እና ፍቅራቸውን አቅርበዋል።

16 Feb 2026, 11:29