ፈልግ

የዩክሬይን እና የራሻ ጦርነት ያስከተለው ውድመት የዩክሬይን እና የራሻ ጦርነት ያስከተለው ውድመት   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መድኃኒትና የቤት ማሞቂያ መሣሪያዎችን ወደ ዩክሬን ላኩ

ዩክሬን በጦርነት ምክንያት ለአራተኛው አመት ጨካኝ እና አሰቃቂ የክረምት ወቅት ስትጋለጥ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የአካባቢው ጳጳሳት ያቀረቡትን ተስፋ አስቆራጭ ልመና ለመመለስ ጣልቃ ገብተዋል፣ በጣም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎችም አስፈላጊ የሕክምና አቅርቦቶችን እና የኤሌክትሪክ ማሞቂያዎችን በጭነት መኪና ልከዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ጦርነቱ የጥፋት መንገድ ማስከተሉን ቀጥሏል፣ ቤተሰቦች ተበታትነዋል፣ ሲቪሎች ለሕይወታቸው እየሸሹ፣ ሴቶችና ልጆች ባሎቻቸው ወደ ጦር ግንባር በመሄዳቸው የተነሳ ከባሎቻቸው ተለያይተው እና ቤቶች ወደ ፍርስራሽነት ተለውጠዋል። ሆኖም፣ በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያት እንኳን፣ የደግነትና የመልሶ ማቋቋም ተግባራት ይንጸባረቃሉ።

በዩክሬን ያለውን ሁኔታ “የሰብአዊ አደጋ” ሲሉ በመግለጽ ከልብ የመነጨ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ አስፈላጊ መድኃኒቶችን በጭነት መኪኖች ልከዋል።

በቫቲካን የበጎ ተግባራት አገልግሎቶች የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከ1 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ዋጋ ያለው እርዳታ በጭነት መኪና ልከዋል፣ ይህም በዋናነት በባንኮ ፋርማሴውቲኮ ETS ፋውንዴሽን የገንዘብ እርዳታ የቀረበ መሆኑም ተገልጿል።

ህክምና እና ሌሎችም

በጦርነት ጊዜ ፍላጎቶች ከህክምና በላይ ይዘልቃሉ። የካርኪፍ-ዛፖሪዥያ ጳጳስ ፓቭሎ ሆንቻሩክ ከ800 በላይ ቤተሰቦችን ወክለው ሲናገሩ፣ ወታደራዊ ጥቃቶች የኃይል መሠረተ ልማቱን ካበላሹ በኋላ ማሞቂያ ሳይኖራቸው የቀሩ ቤተሰቦችን ወክለው አስደናቂ ጥሪ አቅርበዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥገና ማድረግ የማይቻል ስለሆነ ጳጳሱ የማሞቂያ መሳሪያዎችን በማቀረብ በማረጋገጥ ረገድ ተጨባጭ እገዛ ስለተደረገላቸው እጅግ በጣም አመስግነዋል።

የካቲት 17/2018 ዓ.ም ጠዋት፣ ከጣሊያን የተገዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ በዘይት የተሞሉ የኤሌክትሪክ ማሞቂያዎች ወደ ዛፖሪዥዚያ ደርሰዋል። ከ1,000 በላይ የሚሆኑት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች ሙቀት የሚሰጡ መሣርያዎች የተላኩ ሲሆን፣ አንዳንድ ሰዎች በሞቃት መጠለያዎች እና ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች ለመጠለል ተገደዋል።

የሰላም ስጦታ

ይህ እርዳታ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ እሁድ የካቲት 15/2018 ዓ.ም ላቀረቡት ጥሪ የተሰጠ ተጨባጭ ምላሽ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዩክሬን ጦርነት የተጀመረበትን አራተኛ አመት አስመልክተው ተጎጂዎችን፣ “ያዘኑ ቤተሰቦችን” እና “ሊገለጽ የማይችል ስቃይ” አስታውሰው “ሊዘገይ የማይችል” የሰላም አጣዳፊ አስፈላጊነትን ደግመው ተናግረው እንደ ነበረ ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የሰላም ስጦታ በዘመናችን ላይ እንዲበራ” አድማጮቻቸውን ለጸሎት በመጠየቅ አስተያየታቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል።  

 

25 Feb 2026, 15:29