ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአምባሳደሮች የቀረበላቸውን የሹመት ደብዳቤ ሲቀበሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከአምባሳደሮች የቀረበላቸውን የሹመት ደብዳቤ ሲቀበሉ  (@Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ሊዮ 14ኛ፥ አምባሳደሮች እጅግ አስፈላጊ ለሆነው ሰላም አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የቅድስት መንበር ዕውቅናን ያገኙ የልዩ ልዩ አገራት አምባሳደሮችን በቫቲካን ተቀብለው ንግግር አድርገውላቸዋል። ቅዱስነታቸው ለአምባሳደሮቹ ባደረጉት ንግግር፥ ተልዕኳቸው የጋራ ውይይትን እና መግባባትን በማጠናከር በዓለማችን እጅግ አስፈላጊ ለሆነው ሰላም አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚሆን ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ማንኛውም አገር፣ ማኅበረሰብ ወይም ዓለም አቀፍ ሥርዓት ስኬታማነቱን በኃይል ወይም በብልጽግና ብቻ በመለካት በችግር ውስጥ የሚገኙትን ችላ የሚል ከሆነ፥ ፍትሃዊ እና ሰብዓዊ ብሎ ራሱን ሊጠራ አይችልም” ብለው፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ ለድሆች እና ለተረሱት ሰዎች ያለው ፍቅር፥ ለመከራ የተጋለጡትን ችላ እንዳንላቸው እና ማንኛውንም ዓይነት ራስ ወዳድነት እንድንቃወም ያስገድደናል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ግንቦት 13/2018 ዓ. ም. ጠዋት ከሴራሊዮን፣ ከባንግላዲሽ፣ ከየመን፣ ከሩዋንዳ፣ ከናሚቢያ፣ ከሞሪሺየስ፣ ከቻድ እና ከስሪላንካ የተላኩት አዳዲስ አምባሳድሮችን በቫቲካን ተቀብለው ንግግር ካደረጉ በኋላ ከአምባሳደሮች የቀረበላቸውን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።

ለዲፕሎማሲያዊ አንድነት ያለው ራዕይ

ቤተ ክርስቲያን የጴንጤቆስጤ በዓልን ለማክበር መቃረቧን የተናገሩት ቅዱስነታቸው፥ መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርቱ ላይ እንዴት እንደወረደ በማስታወስ፥ ፍርሃትን ወደ ድፍረት እና መከፋፈል ወደ አንድነት በመቀየር በሁሉም ቋንቋዎች እንዲናገሩ በማድረግ እንዴት እንደለወጣቸው አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከአዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ሲቀበሉ
ቅዱስነታቸው ከአዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ሲቀበሉ   (@Vatican Media)

“ተመሳሳይ የአንድነት ራዕይ ዲፕሎማሲያዊ ዓለምን ሊያበረታታ እንደሚችል ተስፋ አለኝ” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ “ይህም በአገሮች መካከል ያለው ገንቢ ግንኙነቶችን በእውነተኛ ግልጽነት፣ በጋራ መከባበር እና የኃላፊነት ስሜት እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል” ብለዋል።

ዲፕሎማሲ አለመግባባቶችን ለማሸነፍ እና መተማመንን ወደቦታ ለመመለስ ያግዛል

በዚህ ረገድ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በጥር መጀመሪያ ላይ በቅድስት መንበር ዕውቅና ለተሰጣቸው ዲፕሎማሲያዊ አካላት ያቀረቡትን ጥሪ እንደገና ማደስ ሲፈልጉ፥ ሰላም በጦር መሣሪያ ኃይል በሚፈለግበት ጊዜ እና የበላይነትን ለማረጋገጥ እንደ ቅድመ ሁኔታ በሚቀርብበት ጊዜ “በሁሉም ደረጃዎች የሁለትዮሽ፣ የክልል እና የብዙ አገራትን የጋራ ውይይት የሚያበረታታ እና ስምምነትን የሚፈልግ ዲፕሎማሲ አስቸኳይ ፍላጎት አለ” ሲሉ በድጋሚ ገልጸዋል።

“እንዲህ ዓይነቱ ውይይት ወደ ሰላም የሚያመሩ መንገዶችን በቅንነት በመፈለግ የሚነሳሳ ነው” ሲሉ ተናግረው፥ ቃላት ሳይዛቡ ወይም ጥላቻን ሳይገልጹ ግልጽ የሆኑ እውነታዎችን ማቅረብን ይጠይቃል” ብለው፥ “አለመግባባቶች ሊወገዱ እና እምነትን በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች አውድ ውስጥ እንደገና መገንባት የሚቻለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው”  ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ውይይት የልብ መለውጥን ይጠይቃል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ “ጨዋነት የተሞላበት ግልጽ ውይይት አስፈላጊ ቢሆንም፥ ጥልቅ የልብ መለወጥ እና ለጋራ ጥቅም ሲባል የተወሰኑ ፍላጎቶችን ወደ ጎን የመተው ፈቃደኛነት አብሮ መኖር አለበት” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ስኬት የሚለካው በኃይል እና በብልጽግና ብቻ ከሆነ፥ በማኅበረሰቡ  የተገለሉትን ችላ የሚል የትኛውም አገር፣ ማኅበረሰብ ወይም ዓለም አቀፍ ሥርዓት ራሱን በእውነት ፍትሃዊ እና ሰብዓዊ ብሎ ሊጠራ አይችልም” በማለት አስጠንቅቀዋል።

“ኢየሱስ ክርስቶስ ለተረሱት ሰዎች ባለው ፍቅር፥ ለችግር የተጋለጡትን እና የደሄዩትን የሚንቅ ሁሉንም ዓይነት ራስ ወዳድነትን እንድንቃወም ይጠይቀናል” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው ለአምባሳደሮቹ ንግግር ሲያደርጉ
ቅዱስነታቸው ለአምባሳደሮቹ ንግግር ሲያደርጉ   (@Vatican Media)

ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ማጠናከር

የዲፕሎማቶች አገልግሎት ራስን የመስጠት የአንድነት መንፈስ መሆኑን የተናገሩት ቅዱስነታቸው፥ ትብብርን ማበረታታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ማጠናከር ለግንኙነት እና ለድርድር ዕድል መፍጠር እንደሆነ አስረድተዋል።

“አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ትብብርን ለማሳደግ አስፈላጊ መሳሪያዎች ሆነው እንደሚቀጥሉ ገልጸው፥ የጂኦፖሊቲካዊ ውጥረቶች ዓለማችንን የበለጠ እየበታተኑት በሚገኙበት በዚህ ወቅት፥ እነዚህን ተቋማት ውጤታማ እና በሰብዓዊ ቤተሰብ አንድነት ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ አሳስበዋል።

ጠቃሚ የሆነ የመተማመን እና የትብብር ድልድይ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አምባሳደሮችን ለአገልግሎታቸው አመስግነው፥ ይህም በአገሮቻቸው እና በቅድስት መንበር መካከል ዋጋ ያለው የመተማመን እና የትብብር ድልድይ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

“የጋራ ጥረታቸው የሁለትዮሽ እና የብዙ ወገን ተሳትፎን እንደገና እንዲነቃቃ እንዲሁም በማኅበረሰቦች  ለተገለሉት እና ለተረሱ ትኩረት እንዲስጥ ጸሎት በማቅረብ፥ ለበለጠ ፍትሃዊ፣ ወንድማማች እና ሰላማዊ ዓለም ጠንካራ መሠረት ለመጣል አብረው መሥራት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ከፍተኛ ፍላጎት ላለው ሰላም አስተዋጽኦ ማድረግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ከከፍተኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመሆን አዲሶቹ አምባሳደሮች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ፥”ተልዕኮአችሁ ውይይትን እና የጋራ መግባባትን የሚያጥናክር እንዲሁም በዓለማችን ውስጥ እጅግ ለሚፈለገው ሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ ይህን” በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል። 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ያደረጉት ንግግር፤

 

21 May 2026, 16:46