ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ጉብኝት ላይ፤ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ጉብኝት ላይ፤   (Vatican Media)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከልን ጎበኙ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ በሮም አቅራቢያ ካስቴል ጋንዶልፎ የሚገኘውን የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከልን ማክሰኞ ግንቦት 11/2018 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ጎብኝተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ማዕከሉን ሲጎበኙ የቫቲካን ግዛት አስተዳደር ፕሬዝዳንት እህት ራፋኤላ ፔትሪኒ ከዋና ጸሐፊዎቻቸው ከሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤሚሊዮ ናፓ እና ብጹዕ አቡነ ጁሴፔ ፑሊሲ-አሊብራንዲ ጋር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሥፍራው ለተገኙት ገዳማውያን እናገዳማውያት፣ ምዕመናን እና ተመራማሪዎች ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል።

ቅዱስነታቸው ከዚህ በፊት፥ የሰው ልጅ ጨረቃን የረገጠበት 56ኛ ዓመት መታሰቢያ በተከበረበት ሐምሌ 13/2017 ዓ. ም. የምርምር ማዕከሉን ጎብኝተው እንደ ነበር ይታወሳል።

የቫቲካን የጠፈር ሳይንስ ማዕከል በሮም አቅራቢያ በምትገኝ ካስቴል ጋንዶልፎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በከተማዋ በሚገኝ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ውስጥ የተለመደውን የሥራ እና የዕረፍት ጊዜያቸውን አሳልፈዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ጉብኝት ላይ፤
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ጉብኝት ላይ፤   (@Vatican Media)

የቫቲካን የጠፈር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ኢየሱሳዊ ካኅን አባ ሪቻርድ አንቶኒ ዲ’ሱዛ እና ተባባሪያቸው ወንድም ጋይ ኮንሶልማኞ በሥፍራው ከተገኙት መካከል እንደ ነበሩ ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በተቋሙ ጸሎት ቤት ውስጥ አጭር ጸሎት ካደረሱ በኋላ ከማዕከሉ ባለሙያዎች እና ምዕመናን ሠራተኞች ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል።

 

21 May 2026, 09:24