የካርዲናሎች የመጀመሪያ ቀን ውይይት በሰላም ላይ በማተኮር መጠናቀቁ ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ዓርብ ሰኔ 19/2018 ዓ. ም. ከሰዓት በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ የተጀመረው ልዩ የካርዲናሎች ስብሰባ፥ በቬንዙዌላ በተከሰተው አሳዛኝ የመሬት መንቀጥቀጥ የተጎዱን በርካታ ሰዎች በጸሎት በማስታወስ ተካሂዷል።
“የኃይል ባህል እና የፍቅር ስልጣኔ” በሚል ጭብጥ የተካሄደው ስብሰባ “ማግኒፊካ ሂውማኒታስ” ወይም “የሰዎች አስደናቂነት” በሚለው ሐዋርያዊ መልዕክት አምስተኛ ምዕራፍ ላይ ያሰላሰለ ሲሆን፥ የተጀመረውም ካርዲናል ፓብሎ ቪርጂሊዮ ሲዮንግኮ ዴቪድ በመሩት የጋራ ጸሎት እንደ ነበር ታውቋል። የመግቢያ ንግግር እንዲያቀርቡ የተጋበዙት በጳጳሳዊ ምክር ቤት የእምነት አስተምህሮ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ብጹዕ ካርዲናል ቪልቶር ማኑኤል ፌርናንደዝ ሲሆኑ፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በስብሰባው መክፈቻ ላይ ከተገኙ በኋላ ለጠቅላላ ስብሰባ ተመልሰዋል።
ጦርነት መደበኛ መሆን የለበትም
በጉባኤው ላይ በተካሄደው ውይይት ላይ አሥራ አንድ ቡድኖች የተገኙ ሲሆን፥ በመጀመሪያው ስብስብ ስምንቱ እና በሁለተኛው ስብስብ ሦስቱ መካፈላቸው ታውቋል። ቡድኖቹ አሁኑ ያሉትን ተግዳሮቶች በመፍታት ረገድ የኃይል ባሕልን የሚያዋርድ ኃይል መኖሩን፣ ሁለንተናዊ ተደራሽነት፣ ከኃያላን አመክንዮ ጋር የመጣጣም ፈተና እና የጦርነት እና የክፍፍል መደበኛነት፣ ይህም መቻቻልን የሚቀንስ እና ግጭቶችን ለመፍታት አደገኛ የሆኑ አቀራረቦችን የሚያበረታታ ነው” ሲል የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል አመልክቷል።
ከዚህ ዳራ አንጻር ተሳታፊዎቹ ሰላምን እና የፍቅር ሥልጣኔን የመገንባት ኃላፊነት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተው በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሰዎች ላይ ያተኮረ ቋንቋን በመጠቀም እምነት የሚጣልበት ምስክርነት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ማዳመጥ፣ ይቅርታ፣ እርቅ፣ መልሶ ማቋቋም፣ ፍትህ እና ተጨባጭ ምልክቶች፥ እንዲህ ዓይነቱ ቋንቋ በግጭት ውስጥ የተዘፈቁትን ሰዎች ልብ መንካት፣ በጦርነት ምክንያት ለተፈጠሩ ቁስሎች እውቅናን በመስጠት እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነትን በመፈለግን ማበረታታት እንደሚችል ተናግረዋል።
ሰላምን የመገንባት ኃላፊነት
ውይይቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነት ለተዓማኒነቷ አስፈላጊ እንደሆነ በማጉላት፥ እንደ ሌሎች እምነቶች እና ሃይማኖቶች በተለይም ከእስልምና እምነት ጋር የሚደረግ ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።
ዓለም አቀፋዊ ግዴለሽነት ሰዎች ለሌሎች ሰዎች ስቃይ ግድየለሽ እንዲሆኑ በሚያደርግበት በዚህ ወቅት እያንዳንዱ ግለሰብ ሰላምን ለመገንባት ኃላፊነት እንዲወስድ የተጠራ መሆኑን አሳስቧል።
በዚህ አውድ ሁሉም ቡድኖች በክርስቶስ እና በወንጌል ላይ የእምነት ማዕከላዊነትን በማረጋገጥ ይህም ዓለምን እንደ ተራ ንድፈ ሐሳብ ከመቁጠር ይልቅ ሕይወት ሲኖር የመለወጥ ኃይል መኖሩን እንዲሁም አንዳንድ ሁኔታዎች በእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ብቻ ሊፈቱ እንደሚችሉ በመጥቀስ፥ የቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያ ጥሪ መሆኑን በመግለጽ፥ በርካታ ቡድኖች ቤተ ክርስቲያን በቅድስት አገር እና በምሥራቅ አውሮፓ ውስጥ ያከናወነችውን ሥራ እንደ ምሳሌ ጠቁመዋል።
የፖለቲካ ሥልጣን ሚናንም ያነሳው ውይይቱ፥ ከኢኮኖሚ ኃይል ጋር ካለው መርዛማ ግንኙነት ቤተ ክርስቲያን ነፃ እንድትወጣ ጥሪ አቅርቦ፥ ሌሎች ርዕሠ ጉዳዮችም ቤተሰብን፣ ትምህርትን፣ ፈጣን መፍትሄዎችን ከመጠየቅ ባሻገር ደፋር የወንጌል አገልግሎት አስፈላጊነትን ያካተተ እንደ ነበር ተመልክቷል። በርካታ ቡድኖች የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲ እና የቤተ ክርስቲያን ድምጽ መሰማቱን በማረጋገጥ ረገድ የቅድስት መንበር ሚናን አጉልተው አሳይተዋል።
ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጥሪ ጋር ለሰላም መቆም
በዚህ አውድ ውስጥ ብዙ ተሳታፊዎች ወንጌል በኃይል ሊጫን ስለማይችል ከትክክለኛው የጦርነት አመክንዮ ባሻገር ተመጣጣኝ ራስን ስለ መከላከል መብት መናገር አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው፥
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሐዋርያዊ መልዕክታቸው የትጥቅ ግጭቶች በማውገዝ ለሰላም ተደጋጋሚ ጥሪ በማቅረባቸው አመስግነዋቸዋል። ውይይቱ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን ከፖለቲካ ሥልጣን ነፃ መሆኗን ለማረጋገጥ እንደ ዋስትና በቀረበው የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ አገልግሎት ምሳሌ (ሙነስ ፔትሪነም) እና እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ የሰላም ምልክቶች ሆነው ሊያገለግሉ የሚችሉ ተምሳሌታዊ ምልክቶች አስፈላጊነት ላይ ተወያይቷል።
ለኃላፊነት የቀረበ ጥሪ
ውይይቱ በጭብጦቹ ላይ በቀረቡ በርካታ የግል አስተያየቶች ላይ ውይይቶችን በማካሄድ ተጠናቋል። አንዳንድ ካርዲናሎች በስብሰባው ወቅት ለተሰጠው የውይይት ዕድል ምስጋናቸውን ገልጸው፥ የፍቅር ሥልጣኔን ለማስተዋወቅ ከሌሎች ሃይማኖቶች መሪዎች ጋር አብሮ የመሥራት አስፈላጊነትን አረጋግጠዋል።
ሌሎች ደግሞ በርካታ ሰዎች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በሐዋርያዊ መልዕክታቸው፥ ቤተ ክርስቲያን ልብን የሚከፍቱ ቃላትን ለመናገር መዘግየቷን በግልጽ በማመናቸው የተሰማቸውን ደስታ እንደገለጹ ተናግረው፥ ካርዲናሎቹ በተጨማሪም ውይይቱ የካርዲናሎች ጉባኤ ሰላምን ለመገንባት ኃላፊነትን እንዲወስድ ጥሪ ማቅረቡን አፅንዖት ሰጥተው፥ ይህም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1986 ዓ. ም. የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአሲሲ ባደረጉት ዓለም አቀፍ የሰላም የጸሎት ተምሳሌታዊ ተነሳሽነቶች አማካኝነት ጭምር መሆኑን አስታውሰዋል።
