ፈልግ

ብጹዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማሊ ብጹዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማሊ  

ካርዲናል ኦማሊ ጾታዊ በደልን በመከላከል ባሕል ተጨማሪ ጥረት መታየቱን ገለጹ

በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሕጻናት ደኅንነት ጥበቃ ኮሚሽን ሚያዝያ 26/2015 ዓ. ም. ባካሄደው ጉባኤ ላይ የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ብጹዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማሊ ያደረጉት ንግግር ሙሉ ይዘት ታትሞ ይፋ መሆኑ ታውቋል።ብጹዕ ካርዲናል ኦማሊ ለጉባኤው ተካፋዮች ባሰሙት ንግግር፣ ከዚህ በፊት የተጀመረውን የኮሚሺኑን ሥራ ለማስቀጠል እና ኮሚሺኑ ከተመሠረተበት፣ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2013 ዓ. ም. ጀምሮ ሲከናወን የቆየውን ተግባር ለማጠናከር መሰብሰባቸውን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ጉባኤውን የሚጀምሩት ፆታዊ ጥቃት ያስከተለውን ክፋት ጨምሮ ሁሉም ዓይነት ሥፍር ቁጥር የሌላቸው በደሎች በቤተ ክርስቲያን እና ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉት ሰዎች ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በማስታወስ እንደሆነ ገልጸው፣ ይህም ልዩ እና የማይተካ ትኩረታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ዋና ትኩረታቸውም በበደል ምክንያት በሕይወታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በማበረታታት የመከላከል እና የመንከባከብ ባሕልን ለማምጣት እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቦታ እንዳይኖረው በትጋት መሥራት መሆኑን አስገንዝበዋል።

1. በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሕጻናት ደኅንነት ታሪክ እና ሁኔታ

በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሕጻናት ጥበቃ ኮሚሽን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2013 ዓ. ም. በዘጠኝ ካርዲናሎች መቋቋሙን የገለጹት ካርዲናል ኦማሊ፣ ቡድኑ ከተዋቀረበት የመጀመሪያ ዋና ምክንያቶች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአካለ መጠን ባልደረሱ ሕፃናት ላይ ከሚደርስ ጾታዊ በደል ጋር በተያያዘ እያደጉ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚያግዙ ምክረ ሃሳቦችን ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሚያቀርብ አካልን ለማቋቋም እንደ ነበር ገልጸዋል። ቡድኑ ከተዋቀረ በኋላ በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰበሰቡ ገልጸው፣ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2022 ዓ. ም. የተቋቋመው ሦስተኛው ባለ ሃያ አባላት ኮሚሺኑ በውስጡ አሥር ወንዶችን እና አሥር ሴቶችን የያዘ እና ከእነርሱም አሥሩ የቀድሞ አባላት እንደነበሩ አስረድተዋል።

ኮሚሺኑ ከተመሠረተ ከ10 ዓመታት በኋላ ሁለት መሠረታዊ የመዋቅር ችግሮች መኖራቸውን ለይተው ማወቅ መቻላቸውን የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ኦማሊ፣ የመጀመሪያው ችግር ከቀውሱ ለመውጣት የሚያግዙ ግልጽ ያልሆነ ትእዛዞች እንደተሰጧቸው ገልጸው፣ ሁለተኛው ችግር፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፆታዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ችግሮችን መፍታት የማይቻል የሚመስል ሥራ እንደተሰጣቸው ብዙዎች ማየታቸውን አስረድተዋል።እነዚህ ሁለት ድክመቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ፍትሃዊ ፍላጎቶችን እና አልፎ ተርፎም ቁጣን የሚቀሰቅሱ ጉዳዮችን በሁሉም ወገን ለመፍታት እገዛን አለማድረጋቸውን ተናግረው፣ በዚህ የተነሳ ኮሚሽኑ ከውስጥም ሆነ ከውጪም ከፍተኛ ትችት ሲሰነዘርበት መቆየቱን ገልጸዋል።

2. ከ 2013-2022 ዓ. ም. የተገኙ ውጤቶች እና የታዩ ተግዳሮቶች

የቅርብ ጊዜ ችግሮችን ወደ ጎን በመተው፣ ኮሚሽኑ ያሳየው ጠቃሚ ግንዛቤ ዕድገት መኖሩን የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ኦማሊ፣ ለተጎጂዎች የማያቋርጥ ድምጽ ከመሆኑ በተጨማሪ ኮሚሽኑ በቤተ ክርስቲያን የፆታዊ ጥቃት አያያዝ ላይ የማይቀለበስ የባሕል ለውጥ መንገድ እንዲከፈት ማድረጉን አስታውሰው፣ ይህ እውነታ ቀላል ግምት ሊሰጠው አይገባም ብለዋል። ቁልፍ ተነሳሽነቶችን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ የካቲት 2019 ዓ. ም. የሁሉም አገራት የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ፕሬዚዳንቶች ስብሰባ በማካሄድ የተፈጸሙ በደሎችን ምስጢራዊ የሚያደርግ አካሄድን በመሻር፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሪፖርቶችን በማዳመጥ እና የአመራር ስልጠናዎች በመላዋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲሰጥ መደረጉን አስታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ የፈውስ ባሕልን በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አውዶች ወይም የተጠቂዎችን መብት በጣሱ ጉዳዮች ላይ ቅጣት መጣልን የሚገልጹ መጽሐፍት እና ሴሚናሮች በኮሚሽኑ አማካይነት ለቤተ ክርስቲያን  አባላት ምክር መሰራጨቱን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ግልጽ ባልሆነው ተልዕኮው በጳጳሳዊ ምክር ቤቶች ውስጥ ስላለው አቋም እና በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ያለውን ትክክለኛ ስልጣን ጥያቄ በተደጋጋሚ በማየት እንደጎርግሮሳውያኑ 2021 ዓ. ም. “ወጌልን ለአሕዛብ ስበኩ” በሚለው ሐዋርያዊ ሕግ የቀረበውን አዲስ ጅምር በማስተዋል ጥንካሬዎችን እና ድክመቶቹን በመገምገም የኮሚሽኑ ሥልጣን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም መደረጉን ገልጸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የኮሚሽኑ አባላት እና ሌሎች ወሳኝ ባለድርሻ አካላት ወደፊት የሚዋቀረው ኮሚሽን እንዴት እራሱን ማደራጀት እንዳለበት የሚመክር ውይይት ተደርጓል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከሰኔ ወር 2021 እስከ ሰኔ ወር 2022 ዓ. ም. በማጠቃለያ ጽሑፍ ተዘጋጅተው በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች ከቀድሞ አባላት ጋር ውይይት በማካሄድ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ቀስ በቀስ ግልጽ ግንዛቤን መጨበጣቸውን ብጹዕ ካርዲናል ኦማሊ ተናግረዋል።

3. በ 2022 ዓ. ም. (እ. ጎ. አ) አዲስ ኮሚሽን ስለ መቋቋሙ

ወንጌልን ስበኩ በሚለው ሐዋርያዊ ሕግ አንቀፅ 78 ላይ የተገለጸው የአሁኑ ኮሚሽኑ ሥልጣን ዋና አካል፣ የቤተ ክርስቲያን አካላት ትክክለኛ ፖሊሲዎችን እና አካሄዶችን እንዲቀበሉ እና እንዲከተሉ የመርዳት ሃላፊነት ያለው መመሪያ በመባል የሚታወቅ መሆኑ ተገልጿል። ሃላፊነቱም የእምነት ጉዳዮችን እንዲከታተል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2003 ዓ. ም. ጀምሮ በተቋቋመው እና በአጭሩ በቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ሥር የሚመራ የተግባር ኮሚሽን ተመድቦ መደበኛ ሥራውን ላለፉት 6 ወራት ሲያካሂድ መቆየቱ ታውቋል። መመሪያዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አዲስ ክስተት እንዳልሆኑ እና የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤቶችም አግባብ ባለው ባሕላዊ መንገድ በልዩ የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ መካተት ያለባቸውን ዋና መርሆችን የማቅረብ ልምድ እንዳላቸው ካርዲናል ኦማሊ ገልጸዋል።

ሀ. ሰፊ ሥልጣን

1  መመሪያዎች፥ ኮሚሽኑ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2011 ዓ. ም. ይፋ በሆነው ሴርኩላር ደብዳቤ መሠረት ዓለም አቀፍ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። ከግንቦት እስከ መስከረም 2015 ዓ. ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ከብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች፣ ከገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ ከኩሪያ እና እንዲሁም ጾታዊ በደል ከደረሰባቸው ቡድኖች ጋር በመሆን አስተያየት የሚሰጡበትን ደብዳቤ ለማሰራጨት በሚቻልበት ማዕቀፍ ላይ ወደ መግባባት ለመድረስ በእነዚህ ቀናት ውስጥ እንደሚወያዩ እና ተሻሽሎ የቀረበው ጠቅላላ መመሪያ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ይፋ ከመሆኑ በፊት በሲኖዶሳዊነት መንፈስ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

2  አቅም ግንባታ

ሁለተኛው የአቅማቸው ምሰሶ በሰው ልጆች ትከሻ ላይ ሸክም እንዳይሆንባቸው በእግዚአብሔር ምክር እንደሚቆም ካርዲናል ኦማሊ ገልጸው፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በሚያዝያ ወር 2022 ዓ. ም. “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” የሚለውን አንቀጽ 2 ጠቅሰው ለኮሚሽኑ አባላት ያሰሙትን ንግግር አስታውሰዋል። በዚህ ዓመት በመጋቢት ወር ላይ የተሻሻለው ሰነዱ በር. ሊ. ጳ. የጸና ሆኑ በየአገራቱ በሚገኙ ጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጽሕፈት ቤቶች ወይም ሌሎች አካላት ዘንድ እንዲኖሩ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ለተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንክብካቤን በማድረግ የሚቀርቡ የውንጀል ክሶችን መቀበል የሚችሉበት መሆኑን አስረድተዋል።

3 ዓመታሪ ሪፖርት

“ትክክለኛ ፖሊሲዎችን በመመሪያነት ማቋቋም እና መርሃ ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም አቅምን ለማሳደግ ቤተ ክርስቲያን መርዳት ቁልፍ መሣሪያዎች ናቸው” ካርዲናል ኦማሊ፣ ስለ ተግባራቸው ያለውን መልካም አሠራር እና ግልጽነት ማክበር የሥራቸው ቁልፍ መመዘኛዎች መሆናቸው ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቀረበው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ መጠቀሱን ገልጸው፣ ዓመታዊ የክትትል ፖሊሲዎች እና አሠራሮች በሪፖርት መልክ ተዘጋጅተው ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የሚቀርቡ መሆኑን አስታውቀዋል። ሪፖርቱ ለህትመት ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ካርዲናል ኦማሊ፣ የኮሚሽኑን እንቅስቃሴ በዝርዝር ከመግለጽ ባለፈ፣ ሪፖርቱ ራሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለውጦችን ለማድረግ የሚያስቻል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥረት የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ለማድረግ ሰፊ ሚና ያለው ሊሆን እንደሚገባ ተናግረው፣ “በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ጾታዊ ጥቃቶችን የመከላከል እና የመጠበቅ እርምጃዎች ላይ ክፍተቶች ወይም ቀጣይ ችግሮች ተለይተው ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

ማጠቃለያ

አዲሱ ኮሚሽን ረጅም ታሪክ ያለው ነገር ግን በስድስት ወራት ብቻ ትላልቅ አጀንዳዎችን በማስቆጠር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ሁሉም እያደጉ ባሉ ህመሞች ውስጥ ቢገኙም ወደ ተጨማሪ የአሠራር ዘዴ እየተሸጋገሩ መሆናቸውን ቢያሳያዩም ትልቅ እመርታ ማምጣታቸው ገልጸዋል። ሁኔታዎችን ለመገምገም እና ለማሻሻል የሚያስችል መመሪያን የተቀበሉ 114 የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች እና የገዳማውያን እና ገዳማውያት ማኅበራት መኖራቸውን ካርዲናል ኦማሊ ገልጸው፣ ስልጠና እንዲሰጥ መርዳት እና አንቀፅ 2ን ለመተግበር ትልቅ ቁርጠኝነት ቢሆንም በጥሩ ሁኔታ የተጀመረ እና ኮሚሽኑ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ከተመሠረተበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በብዙዎች ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ጥበቃ ላይ ከፍተኛ የአመለካከት ለውጥ የታየበት መሆኑን አስረድተዋል።

ተዓማኒነት ያለው እና ሰውን ያማከለ፣ በተለይም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በደል የሚደርስባቸውን ወይም ለአደጋ ሊያጋለጡ ለሚችሉ ጉዳዮች ምላሽ የሚሰጥ ዓመታዊ ሪፖርትን ማቅረብም ትልቅ ጥረት እንደሆነ ገልጸው፣ ለኮሚሽኑ እና ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያደርግ እንደሆነ አስረድተዋል። የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራቶት ትልቅ መሻሻል የታየበት እና ልዩ ልዩ ባለሙያዎች እና በጎ ፈቃደኞችን አዲስ ነገር ሲገጥማቸው ሕመም መሰማቱ የማይቀር ቢኖርም፣ አዲሱ ተልዕኮአቸው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ባለፉት ጊዜያት የተነሱትን አንዳንድ ብስጭቶች የሚፈታ እና የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየን መሆኑን የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ብጹዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማሊ ገልጸዋል።

 

15 May 2023, 18:51