ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት   (AFP or licensors)

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት፡ መንግስታት ትክክለኛ ውይይት ማድረግ አለባቸው አሉ!

ቅድስት መንበር ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታድርገውን ውይይት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊ ሀገራት ባደረጉት ንግግር "የአገልግሎት መንፈስ" ማዳበር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የባለብዙ ወገን ሥርዓት - ማለትም እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የዓለም ንግድ ድርጅት ያሉ ድርጅቶች አንድ ላይ የሚያሰባስቡ እና ውሳኔ የሚያደርጉ ድርጅቶች ሥርዓት ቀውስ ውስጥ ገብቷል በማለት የተናገሩ ሲሆን በዚህ መልኩ ነበር ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በቅርቡ ያደረጉትን ንግግር የጀመሩት።

የሊቀ ጳጳሱ ንግግር - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ሳምንታዊ አጠቃላይ ውይይት ላይ፣ “እምነትን እንደገና መገንባትና ዓለም አቀፋዊ አንድነትን ማደስ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር - ከተሃድሶው ጀምሮ በተለያዩ የቅድስት መንበር ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። የባለብዙ ወገን ሥርዓት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አድልዎ እና እየጨመረ የመጣውን የሃይማኖት ነፃነት ስጋት ላይ ያላቸውን አስተያየት ሰንዝረዋል።

ባለብዙ ወገን መድረኮች እንደ መጋናኛ ቦታዎች

የሊቀ ጳጳስ ጋልገር የመጀመሪያው ነጥብ በባለብዙ ወገን መቼቶች ውስጥ እውነተኛ ውይይት አስፈላጊነትን ያሳስባል።

በእነዚህ መድረኮች “በአንድ ጉዳይ ላይ የየራሳቸውን አቋም ለማስረዳት የቃላት ፍሰት ወንዞች በውክልና ይተላለፋሉ”፣ ነገር ግን “አንድ አገር ሁል ጊዜ በግለሰብ ክልሎች በኩል ለማዳመጥ ተመሳሳይ ፈቃደኛነት አያገኝም” ብለዋል ።

ስለዚህ ክልሎች እና አገራት የሌሎችን ግዛቶች ፍላጎት ለማዳመጥ እና ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ቅድሚያ እንዲሰጡ ሊቀ ጳጳስ ጋልገር አሳስበዋል። የዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን መድረኮች “ዋና ሥራ” በክልሎች መካከል “ትክክለኛ የግንኙነቶች እና የውይይት መድረኮች” መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በጣም ደካማ በሆኑ አገሮች ውስጥ አገልግሎት ላይ ያሉ ግዛቶች

የባለብዙ ወገን ውይይቶች ተሳታፊዎች፣ በተጨማሪም ሊቀ ጳጳሱ በመቀጠል “የአገልግሎት መንፈስን እንደገና ማግኘት” አለባቸው ያሉ ሲሆን ይህም “ማገልገል” የሚለውን ቃል ይወክላል፣  “በህብረተሰባችን፣ በህዝቦቻችን ውስጥ ደካማ የሆኑትን መንከባከብ ማለት ነው። የዚህ የጋራ ቁርጠኝነት አካል፣ ገዥዎች የራሳቸውን ፍላጎት፣ የሚጠብቁትን እና ሁሉን ቻይነት የሚያመልክት የግል ፍላጎት ወደ ጎን መተው አለባቸው ብሏል።

የኑክሌር ስጋት

ሌላው የሊቀ ጳጳሱ ንግግር ጭብጥ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት "የኑክሌር መስፋፋት ከፍተኛ ስጋት" ነበር።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች አጠቃላይ መወገድ ቀንን ለማክበር ባደረጉት ንግግር በዚሁ ጭብጥ ላይ የበለጠ አፅንዖት ሰጥተዋል።

እዚያም “በሚያሳዝን ሁኔታ፣ የኒውክሌር ጦርነት አደጋ ከትውልዶች ከፍተኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ የማይታመኑ የኑክሌር አጠቃቀም ዛቻዎችን እያሳየ ሲሆን የጦር መሳሪያ ውድድርም ያለማቋረጥ ወደ ፊት መሮጡን ቀጥሏል ይህ የዓለም አካሄድ መቀልበስ አለበት። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የኑክሌር ጦር መሣሪያዎችን ሙሉ በሙሉ የማስወገድ የመጨረሻ ግብ ፈታኝ እና ሥነ ምግባራዊ እና ሰብአዊነት አስፈላጊ ነው” ሲሉ አጥብቀው መናገራቸውን አስታውሰዋል።

የአዳዲስ ቴክኖሎጂ አደጋዎች

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ስለ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በተለይም ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አደጋዎች በመወያየት በአጠቃላይ ክርክር ንግግራቸውን ቀጠሉ።

በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ ምጡቅ የሆኑ ኮምፒውተሮች ስርዓቶችን እና ሂደቶችን አጠቃቀም እና ውህደትን በተመለከተ በከባድ የስነምግባር ነጸብራቅ ውስጥ መሳተፍ እና "የእነዚህን መሳሪያዎች አድሎአዊ አጠቃቀም ለመግታት መስራት ያስፈልጋል" ብለዋል። የሰውን ልጅ ከሥራ ውጪ እያደረጉ በመምጣታቸው ሊታሰብበት እንደ ሚገባ ገልጿል።

ሌላው ችግር ገዳይ ራስ ገዝ የጦር መሳሪያ ስርዓቶች (LAWS) በፍጥነት የማልማት ጉዳይ አሳሳቢ ነው ያሉ ሲሆን  ሊቀ ጳጳስ ጋልገር እንዳሉት እንዲህ ያሉ ሥርዓቶችን “በቂ፣ ትርጉም ያለው እና ወጥ የሆነ የሰው ልጅ ቁጥጥር ማድረግ” አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም “የድርጊታቸው ሥነ ምግባራዊ ተፅእኖ ለማየት እና ለመዳኘት በእውነት የሚችሉት የሰው ልጆች ብቻ ናቸው” ብሏል።

ሰብአዊ መብቶች

ሊቀ ጳጳሱ አያይዘውም ዘንድሮ 75ኛ ዓመት የዓለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ሰነድ እና እንዲሁም የቪየና ሰነድ እና የድርጊት መርሃ ግብር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህ ድርብ ዓመታዊ በዓል “በአሁኑ ዓለም ስላለው የሰብአዊ መብቶች እና መከበር መሠረት በጥልቀት እንድናስብ ይጋብዘናል” ብሏል።

ዛሬ “ክብራቸው የተነፈገ፣ የተናቀ ወይም የተረገጠ” ብዙ ቡድኖች እንዳሉ አጽንዖት ሰጥቷል፡- ያልተወለዱ በማሕጸን ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን ማጨናገፍ፣ ትምህርት የተነፈጉ ወይም በቂ ያልሆነ ደመወዝ እንዲከፈላቸው የተገደዱ፣ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ የታሰሩ ወይም የሚሰቃዩ፣ የግጭት ሰለባ ወይም አድልዎ ሰለባ የሆኑ ፣ እና ሌሎች ብዙ አይነት መድሎዎች በዓለማችን ውስጥ ተሰራፍተው እንደ ሚገኙ አክለው ገልጿል።

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር በተለይ በሃይማኖት ነፃነት ላይ የሚደረጉ እገዳዎች ወደ አንድ ሦስተኛው የዓለም ሕዝብ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ እና ቀጥተኛ ስደትን እንደሚያስከትሉ በመግለጽ ትኩረት ሰጥተዋል።

መደምደሚያ

ሊቀ ጳጳሱ ንግግራቸውን ያጠናቀቁት በቅድስት መንበር በተለይም ዩክሬንን፣ ሶሪያን (ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማዕቀብ የአካባቢውን ሕዝብ እንደማይጎዳ እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል። ”)፣ ከሰሃራ በታች ያሉ የተለያዩ ክፍሎች፣ ኒካራጓ፣ አዘርባጃን-አርሜኒያ እና የኢየሩሳሌም ከተማ ጉዳይም አንስተዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያደረጉትን ንግግር በመጥቀስ “የዛሬው ግሎባላይዜሽን ዓለም ሁላችንም እንድንቀራረብ አድርጎናል፣ ሆኖም ግን የበለጠ ወንድማማች እንድንሆን አላደረገንም። በእርግጥም በወንድማማችነት ረሃብ እየተሰቃየን ነው” ብለዋል።

ይህ ሆኖ ሳለ ግን “ከእውነት እና ከልብ ከፈለግን ሰላምን እውን ማድረግ ይቻላል፤ ከፈለግን ግን ሰላም ማስፈን እይቻላል። ሰላምን ማስፈን ደግሞ ግዴት ነው ካሉ በኋላ ሊቀ ጳጳስ ፖል ገላገር ንግግራቸውን አጠናቀዋል።  

28 September 2023, 10:20