ፈልግ

ኢየሱስ ቅድስት ማርታን ሲያገኛት የሚያሳይ ኢየሱስ ቅድስት ማርታን ሲያገኛት የሚያሳይ 

አቶ ቶርኔሊ “የኢየሱስ ሕይወት” የሚለው መጽሐፋቸው ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት እንደሚያግዝ ገለጹ

የቅድስት መንበር መገናኛዎች ርዕሠ አንቀጽ አዘጋጅ አቶ አንድሬያ ቶርኒዬሊ በቅርቡ “የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት” በሚል ርዕሥ ያሳተሙትን መጽሐፍ የሚያነቡ ሰዎች ቅዱሳት ወንጌልን በአዲስ መንገድ ሊለማመዱት እንደሚችሉ ተናግረዋል። መጽሐፉ በውስጡ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ያበረከቱትን የመቅድም ጽሑፋቸውን የያዘ ሲሆን፥ የመጽሐፉ ደራሲ አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ እና የመጽሐፉ ተርጓሚ እህት በርናዴት ሬይስ መጽሐፉን በማስመልከት የመስመር ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በየካቲት 14/2016 ዓ. ም. የተካሄደውን ውይይት ያዘጋጀው የሎዮላ አሳታሚ ድርጅት ሲሆን፥ የቅድስት መንበር መገናኛዎች ርዕሠ አንቀጽ ዋና አዘጋጅ አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ እና በትርጉም ሥራ የተባበሩት እህት በርናዴት ሬይስ፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እንደሚናገሩት ምዕመናን ራሳቸውን በእግዚአብሔር ቃል ይመግቡ ዘንድ መጽሐፉን አግኝተው እንዲያነቡት አደራ ብለዋል። 

‘እራሴን በማስታወሻ ደብተር ውስጥ እንደምገኝ አሰብኩ'

ከፍተኛ ጥበብ መጠቀማቸውን የገለጹት አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ፥ “በወንጌል ትዕይንት ውስጥ ሆኜ የማየውን፣ የምሰማውን፣ ቀለማትን፥ ሽታዎችን እና የአየር ጸባይን በማስታወሻ ደብተሬ ውስጥ እንደምጽፍ ይሰማኝ ነበር” ብለዋል።

"በመጽሐፉ ውስጥ የጻፍኳቸው ትዕይንት፣ ቃላት እና እውነታዎች በሙሉ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተገለጹ እንጂ የእኔ አይደሉም" ብለው፥ ይልቁንም “እነዚያ ትዕይንቶች ዛሬም ታይተው ሕያው እንዲሆኑ ለማድረግ ጥረት አድርጌአለሁ፤ በእኔ እና በእናንተ ላይ እንደተፈጸሙ ስለማስብ መጽሐፉን የሚያነቡ ሰዎች ይህ ሙከራ እርግጥ መሆኑን እንደሚመለከቱ ጠቁመዋል።

እግዚአብሔርን ይበልጥ በመውደድ ሳናቋርጥ ልናገኘው ይገባል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ እንደገለጹት፥ ፍቅር ከሩቅ ሲሆን ፈታኝ እንደሚሆን ነገር ግን በቅርብ የሚደረግ የእርስ በርስ ግንኙነት ፍቅርን ለመፍጠር ቁልፍ እንደሆነ አምነዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደተናገሩት ሁሉ በቅዱስ ወንጌልም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚከሰት አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ፥ “በፍቅር የተሞላ ግንኙነት እርስ በርስ መገናኘትን፣ መቀራረብን፣ ዓይን ለዓይን መተያየትን እና እርስ በርስ መደማመጥን የሚጠይቅ ነው” ብለዋል።

"የቅዱስ ወንጌልን ዋና ተዋናይ ከሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ሊኖረን ይገባል” ብሏል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዱስ ወንጌልን በየዕለቱ እንድናነብ እና ራሳችንን በቅዱስ ወንጌል ታሪኮች ውስጥ እንድናስገባ የሚጋብዙን ለዚህም ነው” ብለው፥ የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ስናዳምጥ እርሱ በእያንዳንዱ ጊዜ ያናግረናል፣ ለሕይወታችን የሚጠቅመንን አዲስ ነገር ይነግረናል” ብለዋል።

ጥልቅ ምናባዊ እና ነባር ነገሮችን መግለፅ

የመስመር ላይ ውይይት ተካፋዮች አንድሬያ ቶርኒሊ እና እህት ቤርናዴት ሬይስ፥ ኢየሱስ ክርስቶስን በወንጌል ውስጥ ማግኘት ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኘናል ሲሉ ተናግረዋል። እህት ቤርናዴትም እንደዚሁ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እንደሚናገሩት፥ “ትዝታዎቻችንን ስናድስ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ለምናደርገው ግንኙነት የበለጠ ክፍት እንሆናለን” ብለዋል።

“ትዝታዎቻችንን ማደስ ከእግዚአብሔር ጋር ለምናደርገው እውነተኛ ግንኝነት ራሳችንን የምናዘጋጅበት መንገድ ነው" ብለው፥ “በዚህ ቅጽበት እርሱ በአካል ባይገኝም ነገር ግን እኛን የሚያነሳሳበት መንገዶች አሉት” ብለዋል። ያ ሊሆን የሚችለው እርሱ በሚገኝበት ርዝመት ወይም የአዕምሮ ንድፍ ላይ ስንሆን ብቻ ነው” ብለው፥ ያንን በእርግጠኝነት ማድረግ የምንችለው በየቀኑ አንድ ወይም ሁለት ሃሳቦችን ከቅዱስ ወንጌል ውስጥ ስንወስድ ነው" ብለዋል።

እህት በርናዴት ስለ መጽሐፉ ገላጭ የወንጌል ክፍሎች ሲናገሩ፥ ደራሲው ታሪኮችን ከራሱ እንደማይጨምር ወይም እንደማይወስድ፥ ነገር ግን ከታሪኩ ጋር እንድንገናኝ የሚረዳን ምናልባት ትንሽ ተጨማሪ አውድ ይፈጥራል” ሲሉ ገልጸዋል። የመጽሐፉ ጸሐፊ ሲ አንድሬያ ቶርኒየሊ አስቀድሞ የተጻፉ የቅዱስ ወንጌል ታሪኮችን በጥንቃቄ በመመልከት ይበልጥ ገላጭ፣ ሕያው እና ተጨባጭ በሆነ መንገድ በመተርጎም በታሪኩ ውስጥ ሌሎች ግንኙነቶችን እንደሚፈጥ አስረድተዋል።

ዋናው የቅዱስ ወንጌል ልብ ምሕረት ነው

የወንጌል እምብርት የሆነውን የቀረጥ ሰብሳቢ የዘኬዎስን ታሪክ ያስታወሱት አንድሬያ ቶርኔሊ፥ ኢየሱስ ታላቅ ምሕረትን አንዳደረገለት ገልጾ፣ በዚህ ታሪክ ውስጥ ምሕረት ምን ያህል ኃይለኛ እንደሆነ በመመልከት “በእግዚአብሔር ፍቅር እና ምህረት ከመነካት የበለጠ ምንም የለም" ብለዋል።

አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ በእነዚህ የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖዎች እና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቃላት በኩል  እንደገለጹት፥ እግዚአብሔር ታማኝ እንደሆነ ዘወትር በግልጽ እናያለን ብለው፥ “እኛ ሳንሆን ነገር ግን ሳያቋርጥ በቃሉ ሊያንጸን በመሞከሩ እግዚአብሔር ታማኝ ነው" ሲሉ ተናግሯል።

ዛሬ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ወንጌላት አጅግ አስፈላጊ ናቸው ያሉት አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ፥ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት አሁን ካልታየ እምነት ያለፈ ታሪክ ብቻ በመሆን ትርጉም የሌለው ይሆናል” ብለዋል።

“በየቀኑ እርስ በርስ መገናኘት አስፈላጊ ነው” ያሉት አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ፥ ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በዓይን እና በድምፅ በተለይም በስቃይ ውስጥ የሚገኙትን መጎብኘት እንደሚገባ አሳስበው፥ አዲስ ያሳተሙት መጽሐፋቸው የቅዱስ ወንጌል ዋና ተዋናይ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማግኘት አንባቢያንን እንደሚረዳቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት”

 

 

24 February 2024, 16:27