ፈልግ

በስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ እየደረሰ የምገኘውን ስቃይ የምያሳይ ምስል በስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ እየደረሰ የምገኘውን ስቃይ የምያሳይ ምስል 

“እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ይራመዳል” የተሰኘው የዓለም የስደተኞች ቀን መሪ ቃል መሆኑ ተገለጸ!

ቫቲካን እ.አ.አ 2024 ዓ.ም ለሚከበረው የዓለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን መሪ ቃል ይፋ ማድረጓ ተገለጸ። እ.አ.አ ከ1914 ጀምሮ የዓለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን ካቶሊኮች በግጭት፣ በስደትና በኢኮኖሚ ችግር የተፈናቀሉትን እንዲያስታውሱና እንዲጸልዩ ዕድል ሰጥቷቸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ለ110ኛው የአለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን መሪ ቃል ይሆን ዘንድ በቫቲካን የቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጽሕፈት ቤት እ.አ.አ በመጪው መስከረም 29-2024 የሚከበረው የዚህ ዓመት የዓለም ቀን መሪ ሃሳብ “እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ይራመዳል” የተሰኘው መሪ ቃል እንደ ሆነ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።  

በመንቀሳቀስ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን

ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለእዚሁ 110ኛው የዓለም የስደተኛ እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን የሚሆን መልእክት እንደሚያስተላለፉ ተገልጿል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በቫቲካን የቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጽሕፈት ቤት ይፋ ባደርገው መግለጫ ላይ  ይህ መልእክት “የቤተክርስቲያኗን የጉዞ አቅጣጫ የሚመለከት ነው”፣ “በተለይም በስደተኛ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ ያተኩራል፣ ይህም “የተጓዥ ቤተክርስቲያንን የወቅቱን አምድ” የሚወክሉ ናቸው ሲል መግለጫው አትቷል።

“ሁሉንም ዛቻዎች እና እንቅፋቶችን በማለፍ በሲኖዶሳዊ መንገድ መከናወን ያለበት መንገድ ነው” ሲል መግለጫው ይቀጥላል፣ “ወደ እውነተኛው አገራችን በጋራ እንድንደርስ። በዚህ ጉዞ ውስጥ፣ ሰዎች በማንኛውም ቦታ እራሳቸውን በሚያገኙበት ቦታ፣ በእያንዳንዱ እርምጃ የእርሱን መመሪያ እና ጥበቃ እያረጋገጠ ከህዝቡ ጋር የሚራመደውን የእግዚአብሔርን መኖር ማወቅ አስፈላጊ ነው። ሆኖም የልባችንን ደጅ በሚያንኳኳ እና የመገናኘት እድል በሚሰጠን እያንዳንዱ ስደተኛ ውስጥ የጌታ፣ አማኑኤል፣ ከእኛ ጋር፣ መኖሩን ማወቅ አስፈላጊ ነው” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የዓለም ቀን 110 ዓመታት

የአለም የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን በየአመቱ በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ በሚገኘው እሁድ ቀን ላይ ይከበራል።

እ.አ.አ በ1914 ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው ይህ በዓል በዓለም ዙሪያ ያሉ ካቶሊኮች በግጭት፣ በስደት እና በኢኮኖሚ ችግር የተፈናቀሉትን እንዲያስታውሱ እና እንዲጸልዩ የሚያበረታታ አጋጣሚ ነበር።

ዝግጅቱን ለማክበር፣ በቫቲካን የቅድስት መንበር የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማትን ለማስፋፋት የሚሰረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የመገናኘት ባሕልን ለማዳበር ዘመቻ ያካሂዳል፣ ይህም በዚህ አመት ጭብጥ ላይ በቪዲዮዎች፣ በመረጃ ሰጪ ነገሮች እና በሥነ-መለኮታዊ ነጸብራቅ ጥልቅ ግንዛቤን ለማስተዋወቅ ይረዳ ዘንድ ታስቦ የሚከናወን ነው።

 

23 February 2024, 13:18