ፈልግ

በካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻዎች ውስጥ ከሚገኙ ፎቶግራፎች መካከል በካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻዎች ውስጥ ከሚገኙ ፎቶግራፎች መካከል  

የቫቲካን ሙዚዬሞች እና ጳጳሳዊ ሕንጻዎች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለማክበር መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

“ማርች 8” ከሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ቀደም ብሎ የቫቲካን ሙዚዬሞች እና የካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻዎች በታሪክ፣ በህብረተሰብ እና በኪነጥበብ ላይ ከፍተኛ ተዋጽዕኖ ያደረጉ ሴቶችን እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻዎች አሻራቸውን ያሳረፉ ሴቶችን ለማስታወስ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በዚህ ዓመትም የቫቲካን ሙዚዬሞች እና በሮም አቅራቢያ የሚገኙት የካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻዎች በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል ላይ እንደሚሳተፉ አታውቀዋል። ረቡዕ የካቲት 13/2016 ዓ. ም. ባወጡት መግለጫ፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ልዩ የሴትነት መብት” ብለው ያስታወሱትን የፈጠራ ዕይታን እና ልበ የዋህነትን ለማጉላት ከየካቲት 28-29/2016 ዓ. ም. ድረስ የሚቀርበውን ዋና ጭብጥ የሚያስረዳ ጉብኝት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ከመቅደላዊት ቅድስት ማርያም እስከ ቅድስት እመቤታችን

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ወደ ቫቲካን ሙዚዬም እና ሲስቲን ጸሎት ቤት በማምራት በልዩ ችሎታቸው ምክንያት በታሪክ፣ በኅብረተሰብ እና በሥነ ጥበብ ላይ የማይሻር አሻራ ያሳረፉ ሴቶችን፥ ከእነዚህም መካከል የቅድስት ማርያም መግደላዊት፣ የሴና ቅድስት ካትሪን፣ የቅድስት ስኮላስቲካ እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስሎችን ይጎበኟቸዋል። ጉብኝቱ ዕድሜያቸው ስድስት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያሏቸው አዳጊ ልጆችን የያዙ ቤተሰቦችን ጨምሮ ለሁሉም ሰው ክፍት እንደሆነ ታውቋል።

በጣሊያንኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የሚታገዙት እነዚህ ጉብኝቶች የስሜት ሕዋሳት እና የአእምሮ እክል ያለባቸው ሰዎች ቀደም ብለው “accessibilita.musei@scv.va” በሚለው የኢሜል አድራሻ ከተመዘገቡ ሙሉ በሙሉ ክፍት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በካስቴል ጋንዶልፎ የነበሩ ሴቶች

እንደዚሁም ከጳጳሳዊ ሕንጻዎች ጋር ተዛማችነት ያላቸውን የካስቴል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ቪላዎችን በ8 ዩሮ ልዩ ቅናሽ የመግቢያ ክፍያ ሴት ታዳሚዎች በሙሉ ጉብኝት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታውቋል።

ልዩ ቅናሹ ለሁሉም ሴቶች የተመቻቸ ሲሆን፥ ዓርብ መጋቢት 29 እና ቅዳሜ የካቲት 30/2016 ዓ. ም. ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት እስከ ማታ አሥራ አንድ ሰዓት ተኩል እና የመጨረሻ መግቢያ ሰዓት አሥር ሰዓት ሲሆን የመጨረሻ ቀን በሆነው እሁድ መጋቢት 1/2016 ዓ. ም. ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተኩል እና የመጨረሻ መግቢያ ሰዓት አሥራ አንድ ሰዓት ሆኖ መርሃ ግብር ተዘጋጅቶለታል።

ጎብኚዎች እና አጋሮቻቸው የጳጳሳዊ ሕንጻዎች ታሪካዊ ስብስቦችን፣ ጳጳሳዊ መኖሪያ ቤቶችን እና የአዲሱ ሙዚየም ቦታዎችን ጨምሮ፣ በግልም ይሁን በአስጎበኚዎች ተመርተው በቅርቡ የተመረቀውን "Castel Gandolfo 1944" የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም መመልከት እንደሚችሉ ታውቋል።

እናቶችን፣ ልጃገረዶችን፣ መነኮሳትን እና አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን የሚያስታውሱ ዝግጅቶች

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጳጳሳዊ ሕንጻዎች ውስጥ በጠንካራ ምሳሌያዊ ጠቀሜታቸው ምክንያት ልዩ ቆይታ እንዲያደርጉ የተፈቀደላቸው እናቶ፣ መነኮሳ፣ ሴት ልጆ እና አዲስ የተወለዱ ሕፃና የሚያሳዩ በርካታ ፎቶግራፎች፣ የድምፅ እና የምስል ምስክርነቶች በኤግዚቪሽኑ ቀርበዋል።

በጉብኝቱ መጨረሻ ላይ ጎብኚዎች ከሕንጻዎች ውጭ የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቀጠል የአትክልት ሥፍራን እና በአቅራቢያው የሚገኘውን የአልባኖ ሐይቅ ገጽታን ማድነቅ እንደሚችሉ ሙዚዬሞቹ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ልዩ ቅናሽ የተደረገባቸውን ቲኬቶች በካስቴል ጋንዶልፎ ከተማ ውስጥ ከሚገኝ እና ከቫቲካን ሙዚዬሞች ጋር ተያያዥነት ካለው የ “ፒያሳ ዴላ ሊበርታ” የትኬት መሸጫ ቢሮ ብቻ መግዛት እንደሚቻል መግለጫው ጨምሮ አስታውቋል።

22 February 2024, 12:40