ፈልግ

በስሎቫኪያ ከሚገኘው ከዝቪር ተራራ ላይ የሚገኘው የማርያም ቤተ መቅደስ በስሎቫኪያ ከሚገኘው ከዝቪር ተራራ ላይ የሚገኘው የማርያም ቤተ መቅደስ 

ቫቲካን በስሎቫኪያ በዝቪር ተራራ ላይ ለሚገኘው የማርያም አዲስ ቤተመቅደስ በይፋ እውቅና ሰጠች!

ቫቲካን በስሎቫኪያ በዝቪር ተራራ ላይ ለሚገኘው የማርያም አዲስ ቤተመቅደስ በይፋ እውቅና ሰጠች! በቫቲካን የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት በሊትማንኖቫ ትንሽ መንደር አቅራቢያ እ.አ.አ በ1990 እና 1995 ዓ.ም መካከል የማርያም መገለጥ ተከስቷል በሚባልበት በስሎቫኪያ ከሚገኘው ከዝቪር ተራራ ጋር የተገናኙትን በርካታ መንፈሳዊ ፍሬዎች የሚያረጋግጠውን የፕሬሶቭ ሊቀ ጳጳስ የባይዛንታይን ስርዓተ አምልኮ የሚከተሉ ካቶሊኮች የእውቅና ደብዳቤ መልኳ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እ.አ.አ በ1990 እና 1995 ዓ.ም መካከል በስሎቫኪያ ውስጥ በሊትማንኖቫ፣ በዝቪር ተራራ ላይ ተከስተዋል ከተባሉት የማርያም መገለጦች ጋር የተገናኙትን መንፈሳዊ ፍሬዎች ከገመገመ በኋላ ባለፈው ዓመት ለታተሙት አዳዲስ ደንቦች ምስጋና ይግባውና በቫቲካን የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት በይፋ ፈቃድ መስጠቱ ተገልጿል።

በቫቲካን የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ የባይዛንታይን ሥርዓተ አምልኮ ለሚከተሉ  ካቶሊኮች የፕረሶቭ ሊቀ ጳጳስ ጆናሽ ጆዜፍ ማክስም ፈቃድ መሰጠቱን የሚገልጽ ደብዳቤ መላካቸው ተገልጿል።

ከሰላሳ ዓመታት በፊት ተፈጽሟል የተባለው ክስተት እንዳለ ሆኖ “በቦታው አዘውትረው የሚጓዙ ምዕመናን ላገኙት ብዙ መንፈሳዊ ፍሬዎች” አድናቆታቸውን በመግለጽ፣ ለቁጥር የሚታክቱ “ቅን እና ጥልቅ ኑዛዜዎች” በመደረጋቸው የተነሳ ብዙ መንፈሳዊ ለውጥ ያመጡ ምዕመናን በመኖራቸው የተነሳ ቤተ መቅደሷ እውቅና እንድታገኝ ላቀረቡት የሊቀ ጳጳሱ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ተዛማጅ መልእክቶቹን ሲመረምር የቆየው በቫቲካን የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት  “የመንፈሳዊ ለውጥ ውድ ግብዣዎችን” እንደያዙ ተናግሯል። እነዚህም እንደ “ኢየሱስ ነጻ ያውጣህ… ጠላታችሁም ኢየሱስ ብዙ ደም ያፈሰሰበትን ነፃነት እንዲገድብባችሁ አትፍቀዱ” የሚሉትን ያጠቃልላል።

ቅድስት ድንግል ማርያም እራሷን እንደ “ደስተኛ” አድርጋ ታቀርባለች እና ምእመናን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቅርን በማወቅ እውነተኛውን የደስታ መንገድ እንዲያገኙ ትጋብዛቸዋለች፡- “ከናለህበት ሁኔታ ጭምር እወድሃለሁ … ደስተኛ እንድትሆን እፈልጋለሁ፣ ነገር ግን ይህ አለም ደስተኛ አያደርጋችሁም" በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስፍራው በመገለጽ መናገሯም ተመስክሯል።

የወንጌል መንገድ የተወሳሰበ እንዳልሆነ በማሳየት ምእመናንን ያበረታታሉ። "እሱ ይበልጥ የዋህ እንድትሆኑ ይፈልጋል" በማለት ማርያም ለምዕመናን፣ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቃላት ተጠቅማ ታስተጋባለች።

በጌታ ደስታና ሰላም ማግኘታችን ሰላምን ለመመስከር እና ለማስፋፋት ያስችለናል ሲል መልእክቱ ያትታል።

ከፍቅር የተነሳ ራሱን የሰጠውን ክርስቶስን በመምሰል ምላሽ እና ተሳትፎን አስፈላጊነት በጌታ ተነሳሽነት ያስቀምጣሉ። ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን መውደድ የምላሻችን ማጠቃለያ እና የእኛ ምልዕት ይሆናል።

በደብዳቤው ላይ፣ ካርዲናል ፈርናንዴዝ የተወሰኑ መልዕክቶች “አንዳንድ አሻሚ እና ግልጽ ያልሆኑ ገጽታዎች” እንደያዙ አምነዋል።

ነገር ግን እ.አ.አ በ2003 ዓ.ም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቫቲካን የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በጉዳዩ ላይ የተገለጸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ባለራዕዮች በተባሉት የውስጥ አተረጓጎም ምክንያት እንደሆነ ይታመናል።

እነዚህ ጥቂት መልእክቶች እራሳቸውን እንደ መገኛ ሳይሆን እንደ ውስጣዊ ልምዶች አድርገው አያቀርቡም። እነርሱን የሚኖሩ ሰዎች በቃላት ሊተረጉሟቸው ይሞክራሉ፣ ይህም የግድ ትክክል ያልሆነ ነገር ይሆናል።

በዚህ ምክንያት ሊቀ ጳጳስ ማክስም “ውዥንብር ሊፈጥሩ እና የየዋዕ ሰዎችን እምነት የሚረብሹትን እነዚያን ጥቂት መግለጫዎች ሳይጨምር” ስብስብ እንዲያትሙ ተጋብዘዋል።

በቫቲካን የእምነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት በድጋሚ እንደገለጸው በላቲን ቋንቋ 'ኒሂል ኦብስታት' (ምንም የምያግደው ነገር የለም) የተከሰሱት ምስሎች ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ትክክለኛነት እውቅና መስጠቱን አያመለክትም፣ ነገር ግን “ይሁን እንጂ የህዝብ አምልኮ እና ምእመናን ከፈለጉ ወደዚህ መንፈሳዊ ሃሳብ ያለ ስጋት ሊቀርቡ እንደሚችሉ” ይፈቅዳል።

በሰሜን ስሎቫኪያ ተራሮች ላይ የምትገኘው የባይዛንታይን የካቶሊክ ባህል ትንሽ መንደር ከሊትማኖቫ በሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሥፍራ ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ንጽሕት እና ብጽዕት” በሚል ርእስ በስፍራው መገለጿ ይታወሳል።

10 Jul 2025, 15:34