ፈልግ

16ኛው የጳጳሳት ጠቅላላ መደበኛ ሲኖዶስ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት 16ኛው የጳጳሳት ጠቅላላ መደበኛ ሲኖዶስ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት   (Vatican Media)

ካርዲናል ግሬች፡- ሦስተኛው ምዕራፍ ሲኖዶሳዊ ሂደት ለቤተክርስቲያን ‘የወደፊ እርምጃ’ ጠቃሚ ነው አሉ

የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች 60ኛ የምስረታ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ይፋ ባደረጉት ጽሑፍ የጳጳሳት ሲኖዶስ ዝግመተ ለውጥን በመከታተል የወደፊቱን ጊዜ ይጠባበቃል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች “ሦስተኛው ምዕራፍ የሲኖዶሱ ሂደት በሲኖዶስ ልምድ እና ግንዛቤ ላይ ተጨማሪ እርምጃ እንዲወስድ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ጥረት እንዲደረግ” ጥሪ አቅርበዋል።

ማበረታቻው የቫቲካን አንዱ አካል የሆነው የጳጳሳት ሲኖዶስ የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት አስመልክቶ በታተመ ማስታወሻ ላይ ነው የተገለጸው።

በማስታወሻው ላይ ብፁዕ ካርዲናል ግሬች የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሲኖዶሳዊነትን “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኅብረት ለማግኘት የሚያስችል እጅግ በጣም ልዩ መንገድ ነው” ብለው እንደ ነበረ የገለጹት ካርዲናሉ እነዚህም አስተያየቶች በአሁኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሊዮ አሥራ አራተኛ ጭምር የተስተጋቡ ሲሆን ባለፈው እሁድ እለት መስከረም 04/2018 ዓ.ም ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ እ.አ.አ በ1965 ዓ.ም የጳጳሳት ሲኖዶስ ለመፍጠር የነበራቸውን “ትንቢታዊ አስተሳሰብ” ያሰመሩበት ሲሆን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ማብቂያ አከባቢ ምስረታውን ማብሰራቸውን ካርዲናል ግሬች አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት የዚህ አካል 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "ለቤተክርስቲያኗ አንድነት እና ተልዕኮ እንደገና ቁርጠኝነትን እንደሚያበረታታ" ተስፋ አድርገዋል።

የቀድም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በመሠረታዊ ደረጃ ላይ ባደረጉት በሦስተኛው የሲኖዶስ ሂደት ውስጥ የሚገኘውን ይህ ተስፋ ካዲናል ግሬች በማስታወሻቸው ገልፀውታል።

ከሀገረ ስብከቱ እና ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጀምሮ እ.አ.አ በ2023 እና 2024 ዓ.ም በቫቲካን በተደረገው ሁለት የስብሰባ ክፍለ ጊዜዎች የተገኙ ሦስት ደረጃዎችን አካትቶ ነበር። እነዚህ ስብሰባዎች የማጠቃለያ ሰነድ አዘጋጅተዋል፤ ካርዲናል ግሬች የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና የክልል የቤተ ክርስቲያን አካላት አሁን እንዲመለከቱት አሳስበዋል።

የጳውሎስ ስድስተኛ “ትንቢታዊ” አስተሳሰብ

ብፁዕ ካርዲናል ግሬች ማስታወሻቸውን የጀመሩት ከጳውሎስ 6ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ  በላቲን ቋንቋ “Motu proprio” በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሚጽፋቸው ሰነዶች፣ የምያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎችን የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል)  በላቲን ቋንቋ "Apostolica Solicitudo" (ሐዋርያዊ ስጋት) በሚለው መልእክታቸው በኩል በይፋ ከመሰረቱት ጀምሮ የሲኖዶሱን መነሻ በማየት ነው።

ይህንን አካል ያቋቋመው ካርዲናል ግሬች እንዳሉት ከሆነ “የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አባቶች ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት” የጳጳሳት ኮሌጅን (ሕብረት) “ለመላው ቤተክርስቲያን በቅዱስ ጴጥሮስ ስልጣን ውስጥ እንዲሳተፍ” ሲል የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ተሳታፊዎች አደራ ባሉት መልኩ የተቋቋመ ነው።  

ካርዲናል ግሬች አክለው እንደ ተናገሩት ከሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ቤተክርስቲያንን “መላውን ኤጲስ ቆጶስ የሚወክል ማዕከላዊ ተቋም፣ በመላው ዓለም ጳጳሳት እና በሮም ኤጲስ ቆጶስ መካከል አንድነትን እና ትብብርን የሚያጎለብት” እና ለእግዚአብሔር ህዝብ ወሳኝ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች እና ጥያቄዎች ላይ “የምክር እርዳታ ለመስጠት የሚችል” እንዲሆን አድርገው እንደ መሰረቱት ያስረዳሉ።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ 16 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዎች፣ 3 ልዩ ጠቅላላ ጉባኤዎች እና 11 ልዩ ጉባኤዎች ተካሂደዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ግሬች ከጉባኤው ጀምሮ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በተለያዩ ጉባኤዎች የተነደፉትን ሃሳቦች ወይም የመጨረሻ ሰነዶች ተቀብለው ከሲኖዶስ በኋላ ሐዋርያዊ ማሳሰቢያዎችን በማዘጋጀት ተጠቅመው “ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት መታደስ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክተዋል” በማለት አስረድተዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለውጥ

ይሁን እንጂ በእነዚህ 60 ዓመታት ውስጥ የጳጳሳት ሲኖዶስ “ትልቅ የዝግመተ ለውጥ ሂደት” አድርጓል ሲሉ ብፁዕ ካርዲናል ግሬች ተናግረዋል። ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሊቃነ ጳጳሳት ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ብለዋል ካርዲናል ግሬች እና በተለይም የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሲኖዶሱን ለኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ ከተዘጋጀው ዝግጅት ደረጃ በደረጃ ሂደቱን ለመለወጥ ፈልገው መላው ቤተ ክርስቲያን የምትሳተፍበት” ሲሉ የጳጳሳት ሲኖዶስን ገልጸው እንደ ነበረ አስታውሰዋል።

ይህም ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር የመመካከር የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን፣ ከዚያም በኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች፣ በአህጉራዊ ጉባኤያት እና በተለመዱት ጠቅላላ ጉባኤዎች የተደረጉትን የተለያዩ የ"ማስተዋል" ደረጃዎችን እ.አ.አ በጥቅምት 2023 እና 2024 በሮም በተካሄደው ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን አድርገዋል።

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ የጳጳሳት ሲኖዶስ ተቋም 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር እ.አ.አ በጥቅምት 2015 ዓ.ም አሁን የመጣውን  ለውጥ አመልክተዋል። ካርዲናል ግሬች አክለውም ሲጽፉ “ሲኖዶሱን ከክስተት ወደ ሂደት የመቀየር ውሎቹን” ወስነዋል ብለዋል።

ይህ "የተገላቢጦሽ" ማዳመጥን ያካትታል፣ ይህም "ሁሉም ሰው የሚማረው ነገር አለው" ሲሉ በማስታወሻቸው ያሰፈሩት ካርዲናል ግሬች በመቀጠል ከህዝቡ፣ ከጳጳሳት ኮሌጅ (ሕብረት)፣ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያለው ግንኙነት  “እያንዳንዱ ሰው ሌላውን ያዳምጣል፤ ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ያዳምጣሉ” ሲሉ ካርዲናል አጥብቀው ገልጸው፣ በመቀጠልም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቃል ከሰባት ዓመታት በፊት እ.አ.አ በመስከረም 15/2025 ዓ.ም የታወጀውን ሐዋርያዊ ሕገ ጋት በላቲን ቋንቋ "Episcopalis Communio" (የጳጳሳት ሕብረት) በዋቢነት አንስተዋል።  

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ወደ ኅብረት የመድረስ ዕድል ያለው መንገድ

ብፁዕ ካርዲናል ግሬች አጽንዖት የሰጡት የቅርብ ዓመታት ተሞክሮ እንደሚያሳየው “የሲኖዶሳዊነት ልምምድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኅብረት ለማግኘት የሚያስችል ልዩ መንገድ ነው” ያሉ ሲሆን “የዚህን ሂደት ውበት እና ኃይል ያገኘነው በ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፎች ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለቤተክርስቲያን የሚናገረውን በመስማት እርስበርስ መደማመጥን በተማርንበት ሊዩ ጊዜ ነው” ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ዝግጅቶች ማስታወስ “ለሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽ/ቤት ታላቅ ደስታ ነው” ሲሉ ካርዲናል አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በተመሳሳይም “ሦስተኛው ምዕራፍ የሲኖዶስ ሂደት በሲኖዶሳዊው ልምድ እና ግንዛቤ ላይ ተጨማሪ ዕርምጃ እንዲወሰድ የተቻለውን ሁሉ እንድናደርግ ጥሪ እየቀረበ ነው ሲሉ በማስታወሻቸው ላይ ካርዲናል ግሬች አስፍረዋል።

18 Sep 2025, 15:22