ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ፤ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ፤ 

ቅድስት መንበር ዘላቂ ሰላምን በልማት እንጂ በወታደራዊ ወጪ መገንባት እንደማይገባ አሳሰበች

በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቁት፥ “የእያንዳንዱ ወታደራዊ ወጪ መጨመር የሰዎችን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚውሉ ሃብቶችን እንደሚወስድ ገልጸዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2024 ዓ. ም. 2.7 የዓለም የወታደራዊ ወጪ መጠን ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን የተናገሩት ሊቀ ጳጳሱ፥ በዓመት ለዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ልዩነት 4 ትሪሊዮን ዶላር እንደሆነ እና ለሰላም ከሚውል እያንዳንዱ ዶላር ሁለቱ ለጦርነት እንደሚውል አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፥ “የባለ ብዙ አገራት አንድነት ለጋራ ጥቅም ያላቸው ራዕይ አሁን ካለው የውትድርና ወጪ መጨመር እና ደካማ የልማት ዕርዳታ ቃል ኪዳን ጋር ይቃረናል” ብለዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2024 ዓ. ም. ወታደራዊ ወጪው ወደ 2.7 ትሪሊዮን ዶላር ቢደርስም ለዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ዓመታዊ የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት በ4 ትሪሊዮን ዶላር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህ ማለት ለሰላም ከሚወጣው እያንዳንዱ ዶላር በላይ ሁለት ዶላር ለወታደራዊ ወጪ እንደሚውል ገልጸው፥ የሰው ሕይወትን ለማስቀጠል ከታሰበው ሃብት ይልቅ ለጥፋት የሚውለው መብለጥ መቀጠሉን ተናግረዋልል።

ባለብዙ ወገንነትን የሚያዳክም የሚጋጭ ሃሳብ (ፓራዶክስ)

“እያንዳንዱ የወታደራዊ ወጪ መጨመር የሰዎችን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት እና ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የሚያገለግሉ ሃብቶችን ይወክላል” በማለት ያስጠነቀቁት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛን በመጥቀስ እንደተናገሩት፥ እነዚህ ሃብቶች በጤና አጠባበቅ፣ በትምህርት ወይም በምግብ ሥርዓት ላይ ከመፍሰስ ይልቅ ሕይወትን እና የወንድማማችነት መንፈስን ወደሚያበላሹ የጦር መሣሪያዎች ወጪ እንዲዛወሩ መደረገቸውን አስረድተዋል። አክለውም እርስ በራሱ የሚጋጭ ይህ ሃሳብ

“የባለ ብዙ አገራት አንድነት የተመካበትን የወንድማማችነት መንፈስ እንደሚያዳክም እና ይህም የዘላቂ ልማት ግቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዳይሳካ የሚያደርግ መሆኑን አስረተዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ላይ በሙላት መታመን

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል የባለብዙ አገራት አንድነትን ለማሳደግ የተገባውን ቁርጠኝነት እንደገና ማደስ እንደሚገባ አሳስበው፥ ይህም ለዘላቂ መፍትሔዎች እጅግ አስተማማኝ መሠረት እንደሚያስገኝ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለባለ ብዙ አገራት አንድነት የተስፋ ብርሃን ሆኖ ማገልገሉን እንዲቀጥ ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል። ግጭት እና መከፋፈል እየተስፋፋ በሄደበት ዓለም ውስጥ “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውይይት እና ትብብር ብቸኛው የሰላም እና የዕድገት ጎዳናዎች ናቸው” የሚል እምነት እንዳለው የገለጹት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፥ ከዚህም በላይ እንዲህ ያለው ትብብር መላው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቁርጠኛ መሆን ያለበትን መንገድ ያሳያል” ብለዋል።

የዕዳ ጫና ክብደት

ለዚህ ሚዛናዊ ላልሆነ አለመመጣጠን ተጨማሪው ችግር የዕዳ ጫና ክብደት ነው” ያሉት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፥ በተለይም በትንሹ ባደጉ አገራት፣ ወደብ የሌላቸው አገራት እና የትንንሽ ደሴት አገራትን በመዋቅራዊ ጥገኝነት እንደሚኮነኑ አስረድተዋል። ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል በሁለተኛው መግለጫቸው፥ “የሁሉ አገራት ሁለንተናዊ ልማት ስኬት እና የእያንዳንዱ አገር ክብር በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውስጥ እንደ እኩል አጋርነት መታየት አለበት የሚለው መርህ አሳሳቢ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ዘላቂ ያልሆነውን የዕዳ ጫናን በማውገዝ የዕዳ መሰረዝ አስፈላጊነትን ደግመው የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል፥ “ይህ በኢዮቤልዩ ዓመት ለቅድስት መንበር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምርጫ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ የሞራል ግዴታ ነው” በማለት አፅንዖት ሰጥቷል። “ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት የሰውን ልጆች የጋራ ጥቅም ለማሳደግ በሚጥር ግብ መመራት አለበት” ብለው፥ ከዚህ አንፃር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአዲስ የጋራ ኃላፊነት ስሜት መጠራቱን ገልጸዋል።

 

13 Oct 2025, 16:25