ካርዲናል ፈርናንዴዝ፥ መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች ኃይሉን እንደሚገልጽ ተናገሩ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
“አንዳንድ ጊዜ ከተፈጥሮ ጋር እርሱ በፈለገው ቦታ የሚነፍስ የመንፈስ ቅዱስ ነፃ ተግባር ለሁሉም ክፍት በሆነ ሚስጥራዊነት እንደሚገለጽ፣ እንደዚህ ያሉ ልምዶች ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት በጥልቀት እንድንቀምስ እንደሚያስችሉ እና ለእግዚአብሔር ያለውን ስሜት እያጣ ባለው የዛሬ ዓለም ውስጥ ፈዋሽ መንገድ ሆነው ማገልገል ይችላሉ” ቅዱስ አጎስጢኖስ ተናግሯል።
እነዚህ በጳጳሳዊ የኡርባኖስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተካሄደው፥ “ሚስጢራዊነት፣ ሚስጥራዊ ክስተቶች እና ቅድስና” በሚል ጭብጥ በተዘጋጀው ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ማለትም ኅዳር 2/2018 ዓ. ም. ከተነሱት ጭብጦች መካከል እንደ ነበሩ ታውቋል።
በቅድስት መንበር የእምነት አስተምህሮ ጳጳሳዊ ምክር ቤት መሪ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ማርቼሎ ሴሜራሮ ባቀረቡት ሰላምታ ሰኞ ኅዳር 1/2018 ዓ. ም. የተጀመረው ጉባኤ ረቡዕ ኅዳር 3/2018 ዓ. ም. የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ የጉባኤው ተሳታፊዎች ሐሙስ ዕለት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ጋር እንደሚገናኙ ታውቋል።
መንፈስ ቅዱስ በታሪክ ውስጥ ራሱን መግለጥ
በቅድስት መንበር የእምነት አስተምህሮ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ ማክሰኞ ዕለት በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በጳጳሳዊ ምክር ቤት የተወሰዱትን ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ክስተቶችን መለየትን የተመለከቱ ደንቦች አስረድተዋል።
እነዚህ ደንቦች “መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሙሉ ነፃነት ይሠራል” በሚሉ ዋና ዋና መርሆዎች ላይ የተመሠረቱ መሆናቸውን አስረድተው፥ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች እንደ መገለጥ ወይም ራዕዮች ባሉ ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ክስተቶች እንኳን ሊገለጥ በሚችል የመንፈስ ቅዱስ ነፃነት ላይ ጽኑ እምነት እንዳለ ይገልጻሉ።
ብጹዕ ካርዲናል ፈርናንዴዝ እንደገለጹት፥ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ወደ 3,500 የሚጠጉ የብጽ ዕና እና የቅድስና ጉዳዮች መታየታቸውን ገልጸው፥ በተመሳሳይ ጊዜ ግን፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ምንጭ ያላቸው ሦስት ወይም አራት መግለጫዎች ብቻ መውጣታቸውን ተናግረው፥ ይህም እንዲህ ዓይነቱን ይፋዊ እውቅናን ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
ብጹዕ ካርዲናል ፈርናንዴዝ አክለውም ዋናው ስጋት አንድ ክስተት ከመለኮታዊ ምንጭ እንደሆነ ከተገለጸ በኋላ መልዕክቶቹ “የተገለጠ ቃል” ተብለው ሊወሰዱ የሚችሉበት ሁኔታ እና እንዲህ ዓይነቱ መግለጫ ስለ ትክክለኛነት ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆንን እንደማያረጋግጥ ገልጸው፥ በቤተ ክርስቲያን እውቅና ባገኙ ጉዳዮች ሳይቀሩ ምእመናን ለማመንም ሆነ ላለማመን የግል መገለጦች ሆነው መቀጠላቸውን አስረድተዋል።
የቤተ ክርስቲያን መግለጫ ጥንቃቄ የሚደረግበት እና በብዙ አጋጣሚዎች በርካታ መገለጫዎች ያለ ይፋዊ እውቅና ቅድስናን እና መንፈሳዊ ፍሬዎችን እንደሚያስገኝ ገልጸዋል። ማስተዋል ወደ ስህተት እና ወደ ከባድ ጥቃት ሊያመሩ የሚችሉ ክስተቶችን ለመለየት ይረዳል ብለዋል።
የእምነት አስተምህሮ ምክር ቤት ደንቦች አንድን ክስተት የበለጠ ውስብስብ ወደሚያደርግ ደርጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ጥንቃቄ ሊወሰዱ የሚችሉ ሃሳቦችን እንደሚያቀርቡ ገልጸው፥ አንዳንድ ጉዳዮች በአካባቢው ሊፈቱ የሚችሉ፥ ሌሎች ደግሞ ጥንቃቄ የተሞላበት ማስተዋልን የሚጠይቁ በመሆናቸው የምክር ቤቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ በቅድስት መንበር የእምነት አስተምህሮ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ፈርናንዴዝ ንግግራቸውን ደምድመዋል።
በመካከለኛው ዘመን የሴቶች ምሥጢራዊ ሰዎች
የፓሪስ ኤክስ-ናንቴሬ ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛው ዘመን የክርስትና ታሪክ ጸሐፊ ፕሮፌሰር አንድሬ ቫውቼዝ “በመካከለኛው ዘመን መጨረሻ በምዕራቡ ዓለም ሚስጥራዊነት እና ቅድስና” በሚል ርዕስ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ንግግር አድርገዋል።
ከ12ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ ሚስጥራዊነት፥ ሴትነት እና ዓለማዊነት ድርብ ሂደቶችን ማካሄዱን ገልጸው፥ ይህም አንዳንድ ጊዜ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አጠራጣሪ የሚመስል የግል ተሞክሮ እንደሚሆን እና እንደነዚህ ዓይነት ጸጋዎችን ለተቀበሉ ሰዎች የክህነት አገልግሎት አስፈላጊ እስከማይመስል ድረስ መሄዱን አስረድተዋል።
አንዳንድ የታሪክ ምሁራን የሚስጥራዊነት ተሞክሮን በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች የላቲን ቋንቋ የማያውቁ እና ልምዶቻቸውን ለካኅናት መንገር ለሚኖርባቸው ሴቶች እንደ “መጠጊያ” አድርገው ተርጉመውታል።
ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ግን የተወሰኑ የሃይማኖት ሥርዓቶች በተለይም ፍራንችስካውያን እና ዶሚኒካኖች ሴቶች በእውነቱ ስለ እምነት ምስጢራት ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንደሚያደርጉ አጥብቀው ይናገሩ እንደ ነበር ገልጽው፥ ምክንያቱም “በጊዜያዊ ጉዳዮች ወይም በምሁራዊ አስተሳሰብ” እንዳልተጫኑ አስረድተዋል።
በ14ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ሁኔታው የበለጠ ተሻሽሎ እንደ ነበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኡርባን አምስተኛ እና ግሬጎሪ 11ኛን ጨምሮ ብዙ ክርስቲያኖች እንደ ስዊድን ቅድስት ብሪጅት፣ የሲዬና ቅድስት ካትሪን እና የሞንታው ብፁዕ ዶሮቲያ ያሉ ሰዎች ራዕይ እና ትንቢታዊ ንግግር ቤተ ክርስቲያኗን በፈተና እና በችግር ጊዜ ሊደግፍ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል።
ምስጥራዊነት እንደ መለኮታዊ ‘ስጦታ’
በሰሜን ጣሊያን የሥነ-መለኮት ፋኩልቲ የመንፈሳዊነት እና የመንፈሳዊ ሥነ-መለኮት ታሪክ ፕሮፌሰር አባ ሉካ ኤዚዮ ቦሊስ፥ “ምስጥራዊነት እና ሥነ-መለኮት፥ ውስብስብ እና ፍሬያማ ግንኙነት” በሚለው ርዕሥ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አባ ቦሊስ ይህንን ግንኙነት ለማብራራት ባቀረቡት አስደናቂ ዘይቤ፥ “መብላት” የሚለው ሥነ-መለኮታዊ እውቀትን የሚወክል እና “ምግብን መቅመስ” በሚለው መካከል ያለው ልዩነት ምስጢራዊ ተሞክሮን የሚያመለክት መሆኑን ተናግረው፥ ይህ ልዩነት እምነት ብዙውን ጊዜ ከምክንያት ጋር በተያያዘ ‘በህዳግ አካባቢ’ ተብሎ በሚወሰድበት በእምነት እና በምክንያት መካከል ያለውን ሰፊ ውጥረት ያንፀባርቃል” ብለዋል።
እንዲህ ዓይነቱ መለያየት ሁለቱንም አዳክሟል ሲሉ አባ ቦሊስ ተናግረው፥ ሥነ-መለኮት አንዳንድ ጊዜ ስለ ክርስቲያናዊ መገለጥ ባለው ግንዛቤ ረቂቅ ሆኖ እንደቆየ ገልጸው፥ መንፈሳዊ ተሞክሮ ደግሞ “በሰሚነት ዝንባሌ” አደጋ ላይ መውደቁን በማስረዳት፥ ለዘመናት ከቆየ ጥርጣሬ በኋላ ምስጥራዊነት እንደገና ዋጋ እየተሰጠው እንደሆነ፥ በሕክምና መንገድም ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ያለው ስሜት እየቀነሰ ወደ ሄደበት ዘመን ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
አባ ቦሊስ ምስጥራዊነት ከኢ-ምክንያታዊነት፣ ከግልጽነት፣ ከአጉል እምነት እና ከአስማት ጋር እኩል እንዳልሆነ አፅንዖት ሰጥተው፥ ይልቁንስ፣ መለኮታዊ ስጦታ የጸጋ ፍሬ እንደሆነ እና በቴክኒካዊ መንገድ ሊገኝ የሚችል አለመሆኑን አስረድተዋል።