ብፁዕ ካርዲናል ኮች ር.ሊ.ጳ. ዮሃንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለመጀመሪያ ጊዜ የአይሁዳዊያንን ምኩራብ የጎበኙበትን 40ኛ ዓመት አስመልክተው መግለጫ ሰጡ
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
እ.አ.አ. ሚያዝያ 13 ቀን 1986 ዓ.ም. የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሮም ምኩራብ ጉብኝት እጅግ አስደናቂ ክስተት እንደነበር የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮች፥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሮም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለአይሁድ ሃይማኖት እና ለአይሁድ ሕዝብ ያላቸውን አድናቆት በዓለም ፊት ለመመስከር ወደ ምኩራብ መግባታቸውን አክለው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሃንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር “የአይሁድ ሃይማኖት ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ‘ባዕድ’ ሳይሆን፥ ነገር ግን በተወሰነ መልኩ ለእኛ ሃይማኖት ‘የቅርብ’ ስጦታ ነው” በማለት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ሃይማኖቶች በተለየ መልኩ ከአይሁድ እምነት ጋር ግንኙነት እንዳላት አጽንዖት ሰጥተው ገልጸው የነበረ ሲሆን፥ “አይሁዳውያን ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው” ያሉት ብፁዕነታቸው በዚህም “በጉባኤው የተገለጸውን” በተሳካ ሁኔታ ጠቅለል አድርገው መግለፃቸውን ካርዲናሉ አስረድተዋል።
በተለይም ከአርባ ዓመታት በፊት በነበረው በዚህ የሮም ምኩራብ ጉብኝት፣ እንዲሁም በካቶሊክ እና በአይሁድ ሃይማኖቶች መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ በሚሰጡት ሌሎች በርካታ ጠቃሚ መግለጫዎች፣ የተለያዩ ልብ የሚነኩ ንግግሮቻቸው እና ከአይሁድ ሕዝብ አባላት ጋር በነበራቸው ግላዊ ወዳጅነት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና በአይሁድ እምነት መካከል ለሚደረገው የወደፊት ዕርቅ ትልቅ ትርጉም ያለው መሰረት መጣላቸውን ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮች ገልጸዋል።