ፈልግ

ብጹዕ አቡነ ሩዴሊ፥ ቅድስት መንበር ከሸለመቻቸው 13 አምባሳደሮች ጋር  ብጹዕ አቡነ ሩዴሊ፥ ቅድስት መንበር ከሸለመቻቸው 13 አምባሳደሮች ጋር  

ቅድስት መንበር ዕውቅና የሰጠቻቸው 13 አምባሳደሮች የክብር ሽልማቶች መቀበላቸው ተገለጸ

አገራቸውን በመወከል በቅድስት መንበር ለሁለት ዓመታት ያገለገሉ 13 አምባሳደሮች የቫቲካን ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ የክብር ሽልማት ተቀብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከቅድስት መንበር እውቅና ለተሰጣቸው እና በቫቲካን ቢያንስ ሁለት ዓመታት የኃላፊነት ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ አምባሳደሮች ረቡዕ ግንቦት 5/2018 ዓ. ም. የክብር ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ምርጫ የመጀመሪያ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ አርማን እና በብራና የተዘጋጁ ኦፊሴላዊ የምስክር ወረቀቶችን ለ13 ዲፕሎማቶች የሰጡት በቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት የጠቅላላ ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፓውሎ ሩዴሊ እንደ ነበሩ ታውቋል።

ለአምባሳደሮቹ የተሰጧቸው ሽልማቶች የፒዮስ ዘጠነኛ የብሪታኒያ ንጉሣዊ ቤተሰብ ከፍተኛ ማዕረግ ሲሆን፥ ይህም ቅድስት መንበር ለዲፕሎማሲያዊ አገልግሎት ከምትሰጣቸው ከፍተኛ የክብር  ሽልማቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ታውቋል።

 

14 May 2026, 16:25