ፈልግ

በግዙፍ ‘ስክሪን’ ላይ የሚታይ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ምስል በግዙፍ ‘ስክሪን’ ላይ የሚታይ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ምስል 

ቅድስት መንበር፥ በግዙፍ ‘ስክሪኖች’ አማካይነት ዕለታዊ ዝግጅቶቿን ለማሰራጨት መዘጋጀቷ ተገለጸ

የቅድስት መንበር መገናኛ ጽሕፈት ቤት “Selfiestreet” ከተሰኘ ዲጂታል መድረክ ጋር በመተባበር በሮም እና ሚላን ከተሞች ባሉ ታዋቂ ሥፍራዎች ይፋዊ የቫቲካን ምስሎችን እና መልቲሚዲያ ይዘቶችን ለማሰራጨት መዘጋጀቱ ተነግሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ጽሕፈት ቤቱ፥ ‘Selfiestreet’ ከተሰኘ የጣሊያን ዲጂታል ኔትወርክ ጋር በመተባበር ከቅድስት መንበር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ይፋዊ የምስል መረጃዎችን በግዙፍ ዲጂታል ስክሪኖች አማካይነት ለማሰራጨት ያለመ አዲስ ተነሳሽነት ይፋ አድርጓል።

መርሃ ግብሩ ከእሑድ ግንቦት 9/2018 ዓ. ም. ጀምሮ በሮም እና ሚላን ከተሞች በግልጽ በሚታዩ የሕዝብ መሰብሰቢያዎች ላይ በቪዲዮ የተደገፉ ልዩ ዕለታዊ ስርጭቶችን እንደሚያቀርብ ታውቋል።

ተነሳሽነቱ የቅድስት መንበርን ድምጽ እና ተግባራት በዘመናዊ የዲጂታል መገናኛዎች በኩል ለበርካታ ታዳሚዎች ለማቅረብ እንደሆነ ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ወራትም በሌሎች የጣሊያን ከተሞች ውስጥ በተጨማሪ ስክሪኖች አማካይነት ስርጭቱ ቀስ በቀስ እንደሚሰፋ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ይህም የቫቲካን መረጃን ከባሕላዊ የሚዲያ መድረኮች ባሻገር የበለጠ በስፋት ለማሰራጨት እንደ ሆነ ተገልጿል።

ትብብሩ የተጀመረው ቀደም ሲል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2025 ዓ. ም. በተከበረው የብርሃን ልደቱ በዓል ወቅት ሲሆን፥ በጊዜው የተመረጡ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14 ምስሎች እና ብርሃነ ልደቱን የተመለከቱ መልዕክቶች በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አቅራቢያ በሚገኙ ግዙፍ የዲጂታል ስክሪኖች ላይ መታየት በጀመሩበት ጊዜ እንደ ነበር ይታወሳል።

 

14 May 2026, 16:30