ፈልግ

በኢየሩሳሌም የሚነሳ የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት በኢየሩሳሌም የሚነሳ የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት  (AFP or licensors)

በኢየሩሳለም ቅዱስ ሥፍራዎችን ለማስተዳደር የሚያስችል ደንብ ማጽደቅ ይቻላል ተባለ

በኢየሩሳለም ከተማ ጥንታዊ በሚባሉ መንደሮች በተደረገው የእግር ጉዞ ወቅት በእስልምና እና በአይሁድ እምነት ተከታዮች መካከል ያለፈው እሑድ ግንቦት 21/2014 ዓ. ም. ሁከት መቀስቀሱ ሲነግር በዚህ ምክንያት ከተማዋ ሳትረጋጋ መዋሏ ታውቋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ “ቅዱስ ሥፍራዎችን ለማስተዳደር የሚያስችል ዓለም አቀፍ ዋስትናን በድጋሚ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው” በማለት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ጠበብት አቶ ማሲሞ ዴ ሌዮናርዲስ ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

እ. አ. አ. በ1967 ዓ. ም. ከስድስት ቀናት ጦርነት በኋላ እስራኤል የኢየሩሳሌምን ከተማ ሉዓላዊነት ለማክበር የባንዲራ ቀንን በማወጅ የእግር ጉዞን ስታስተባብር መቆየቷ ይታወሳል። ያለፈው እሑድ በኢየሩሳሌም ከተማ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተቀሰቀሰው አመጽ ጥንታዊ ከሚባለው ከአረብ መንደር ጀምሮ እስከ ደማስቆ በር ድረስ ባለው የፍልስጤማውያን ሠፈር መካሄዱ ታውቋል።

በእስራኤል ጋዜጦች ዘገባ መሠረት በኢየሩሳሌም ከተማ ጥንታዊ መንደሮች በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ወደ 25,000 የሚጠጉ ሰዎች መሳተፋቸው ታውቋል። የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ያይር ላፒድ የእስራኤላውያን የቀኝ ፖለቲካ አራማጅ ታጣቂዎችን በመጥቀስ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን፣ የፍልስጤም ቀይ መስቀል በበኩሉ በጥንታዊው የከተማይቱ መንደር በተፈጠረው ሁከት ወደ 40 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን መቁሰላቸውን አስታውቋል።

በዌስት ባንክ ውስጥ

መስጊድ በሚገኝበት አካባቢ በፖሊስ ሃይሎች እና በፍልስጤማውያን መካከል አዲስ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በዌስት ባንክ በናብሉስ አካባቢ አንዳንድ ፍልስጤማውያን የእስራኤልን ባንዲራዎችን በማቃጠል ረብሻ ማስነሳታቸው ሲነገር፣ በዚህ ወቅት የእስራኤል ጸጥታ አስከባሪዎች አስለቃሽ ጭስ መበተናቸው ታውቋል። በዚህ ወቅት የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማሐመድ አባስ ቃል አቀባይ የሆኑት አቡ ማዘን “ምስራቅ ኢየሩሳሌም እስላማዊ እና ክርስቲያናዊ ቅዱስ ሥፍራዎችን በማካለል ለዘለዓለም የፍልስጤም ግዛት ዋና ከተማ ሆና ትቀጥላለች” በማለት በድጋሚ ተናግረው፣ “እስራኤል በሕዝባችን ላይ፣ በመሬታችን እና በተቀደሱ ቦታዎቻችን ላይ እንደ አገር ሆነን መኖር እስካፈቀደች ድረ በአካባቢው ፀጥታና መረጋጋት ሊገኝ አይችልም” በማለት ተናግረዋል።

ከዮርዳኖስ በኩል

እሑድ ግንቦት 21/2014 ዓ. ም. በኢየሩሳሌም ከተማ ጥንታዊ መንደሮች ውስጥ ለተፈጠረው ሁከት ተቃውሞን የገለጸው የዮርዳኖስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ "በእስራኤል ፖሊስ ሽፋን የተካሄደው የአክራሪዎች ወረራ እና ቀስቃሽ ባሕሪ ታሪካዊ የሕግ ማዕቀፍን እና የዓለም አቀፍ ሕግን እንደሚጥስ፣ እስራኤል የጸሎት ሥፍራ ቅድስናን ማክበር አለባት” በማለት የዮርዳኖስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

በኢየሩሳሌም ከተማ የሚገኙ ጥንታዊ እና አዲስ መንደሮች

በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማሲሞ ዴ ሊዮናርዲስ እንደሚሉት፣ በዩክሬን ውስጥ የሚክሄደው ጦርነት እንደ እስራኤል እና ፍልስጤም ባሉት አገሮች ውስጥ ያሉ ሌሎች ጉዳዮች ችላ እንዲባሉ ማድረጉን ገልጸው፣ ለአሥርተ ዓመታት ሲፈጸሙ የነበሩ ጉዳዮች በማስታወስ የኢየሩሳሌምን ሁኔታ በመጥቀስ ከፍተኛ ውጥረት የሚታይበት አጋጣሚ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ የታዩ ዕድገቶችን የጠቀሱት አቶ ደ ሊዮናርዲስ፣ የፍልስጤም ጉዳይ ተረስቶ መቆየቱን ገልጸው፣ በአንዳንድ አረብ ሀገራት እና በእስራኤል መካከል የነበረው ግንኙነት ወደ መደበኛ ሁኔታ መቀየሩን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤምባሲያቸውን ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ለማዘዋወር መወሰናቸውን በወቅቱ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዮሴፍ ባይደን እንደገና አለመታየቱን አስታውሰዋል።

የሁሉ ሰው ትኩረት በዩክሬን ጦርነት ላይ ሆነ

በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት እና በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ታይቶ ​​የማይታወቅ የምግብ እጥረትን ሊያስከትል ከሚችለው የዩክሬን ወይም የሩሲያ የእህል ንግድ እገዳ በተጨማሪ በእስራኤል እና በፍልስጤም መካከል ያለው ችግር በዩክሬን ውስጥ ከሚካሄድ ጦርነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው እንዳልሆነ ገልጸው፣ ዓለም አቀፍ ዋና "ተዋንያን" በሌላ ጉዳይ ላይ መሰማራታቸው ውጥረቶች እንደገና ብቅ እንዲሉ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢየሩሳሌም ሁኔታ

የኢየሩሳሌምን ሁኔታ በተመለከተ የተነሳው ጥያቄ ውስብስብነት ያለው መሆኑን የገለጹት አቶ ዴ ሊዮናርዲስ ቅድስት መንበር ባለፈው ክፍለ ዘመን ሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ ዓለም አቀፋዊ አሰራሮችን ታስብ እንደነበር አስታውሰው፣ ዛሬ ግን ዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ ባይድረስም ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቅዱስ ሥፍራዎች አያያዝ የሚቆጣጠር ደንብ እና ዋስትና ላይ ሊደረስ እንደሚቻል ገልጸዋል።

31 May 2022, 17:35