ፈልግ

በእህቶች የሚመራ የተግባር መርሃ ግብር በእህቶች የሚመራ የተግባር መርሃ ግብር 

ከኮንራድ ሂልተን መንፈስ ጋር ተመሳሳይ የሆኑት ሃይማኖተኛ ሴቶች ናቸው

የመጀመሪያው የሆቴሉ መስራች የሆነው ኮንራድ ኤን ሒልተንን ሰፊ ራዕይ የነበረውን ከማስተዋወቅ እና ከማሳደግ ይልቅ ፋውንዴሽኑ ለምን ሃይማኖተኛ ሴቶች ላይ ብቻ ትክረቱን እንዳደረገ ሲጠየቅ ፥ “እህቶች ሰፊ ተደራሽነት አላቸው ፥ በዓለም ዙሪያ በችግር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን አጅበው የሚሄዱ እና የሚያግዙ እነሱ ናቸው ፤ አብረዋቸው ይሄዳሉ፣ ያጽናኗቸዋል። ነገር ግን ይህ ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት ያለው ህይወት እንዲገነቡ ይረዷቸዋል ፥ በስራ ክህሎት ስልጠና ያሠለጥኗቸዋል፣ ለራሳቸው ገቢ የሚያገኙበትን መንገድ ለመዘርጋት ይረዷቸዋል። ይህ ደግሞ ከአቶ ሂልተን የስራ ፈጠራ መንፈስ ጋር የሚስማማ ነበር። ስለዚህ እህቶች ለሂልተን አስፈላጊ የሆነውን ብዙ ገፅታዎችን የሚያሰባስቡ ይመስለኛል” ብሏል አቶ ማርክ ሆሊ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ - አዲስ አበባ

የኮንራድ ሂልተን ውርስ

ማርክ ሆሊ ስለ መስራቹ ሲናገር “ኮንራድ ሂልተን በጣም ሃይማኖተኛ እና የጸሎት ሰው እንደነበር ፥ ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ በካቶሊክ እህቶች አስተዋፅዖ ልቡ ተነክቶ እንደነበር እና ፥ በመሆኑም በመጨረሻው ኑዛዜው ፥ እህቶች በተለየ መልኩ ከዕርዳታ ፋውንዴሽኑ ጥቅም ሊያገኙ እንደሚገባ ገልጾ እንደነበር አብራርቷል።

አራቱ የገንዘብ ድጋፍ ቦታዎች

ማርክ ፋውንዴሽኑ በሴት ሃይማኖተኞች በኩል በገንዘብ የሚረዳቸው በህፃናት እና በቤተሰብ ዙርያ ለሚሰሩ አራት የተለያዩ ‘የስትራቴጂ ቦታዎች’ እንዳሉ ገልጿል። የመጀመሪያው ይላል ማርክ ፥ መደበኛ ትምህርት የሚሰጥበት እና የእህቶች ወይም ሲስተሮች የሚበቁበት ቦታ ሲሆን ፥ አክሎም “እነዚህ የገንዘብ ድጋፎች በጉባኤዎች ዘላቂነት እና አረጋውያን እህቶችን የመንከባከብ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ነው።

በተጨማሪም ድርጅቱ በሴት ሃይማኖተኞች በኩል በልጆች እና ቤተሰብ ዙርያ ለሚሰሩ ስራዎች የሚደረጉ ድጋፎች ሲሆኑ ፥ ከዛም ባለፈ የሰዎች ዝውውርን ለማስቆም እና የተረፉትን እንዲያገግሙ እና የብልጽግና ህይወት እንዲገነቡ መርዳት የሚያስችል ድጋፍም ይደረጋል ሲል ገልጿል። ሌላኛው የድጋፍ መስክ እህቶች ማህበረሰባቸውን ለማገዝ በሚያደርጉት ጥረት ድምፃቸውን ለማሰማት ያለመ ነው።

ሌላኛው እና አራተኛው የድጋፍ መስክ ፥ በምርምር እና ግምገማ አካባቢ ለሚሰሩ ሥራዎች ነው ይላል ማርክ፥ በመቀጠልም ‘እህቶች እያደረጉት ስላለው ታላቅ አስተዋጽዖ ስናውቅ ፥ እኛ ወደምናቅደው ነገር እንዲሁም ወደ ሥራቸውም መመለስ ይቻላል’ ብሏል።

የጴንጤቆስጤ ፕሮጀክት

‘ዲካስቴሪ ፎር ኮሙኒኬሽን’ የተባለው ቢሮም እንዲሁ በኮንራድ ኤን ሂልተን ፋውንዴሽን ስር የካቶሊክ እህቶች ማህበር ተጠቃሚ ነው። ዲካስቴሪው የጴንጤቆስጤን ፕሮጄክት የጀመረው ከዚው ፋውንዴሽን ባገኘው ስጦታ ነው። ሴት ሃይማኖተኞቹ ለአንድ ዓመት በነፃ L'Osservatore Romano በሚባለው በጣሊያንኛ ቋንቋ በየቀኑ ጋዜጣ በሚያወጣ የህትመት ድርጅት ውስጥ መመዝገብ ችለዋል ፥ አንዳንድ እህቶችም በሮማ በሚገኙ የዲካስተሪው ቢሮዎች የመግባቢያ ትምህርቶችን ያገኛሉ፣ ሌሎች ደግሞ በመግባቢያ ትምህርት የኦንላይን ስልጠና ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም የዲካስተሪው የእህቶችት ፕሮጀክት በ10 ቋንቋዎች በየሳምንቱ አንድ መጣጥፍ ፥ ሴት ሃይማኖተኞቹ ስለሚሠጡት አገልግሎት የሚገልጽ ፅሁፍ ይቀርባል ተብሏል።

22 March 2023, 17:11