ፈልግ

በእስራኤል 11ኛ ሳምንት ያስቆጠረው ተቃውሞ በእስራኤል 11ኛ ሳምንት ያስቆጠረው ተቃውሞ   (AFP or licensors)

በእስራኤል 11ኛ ሳምንት ያስቆጠረው ተቃውሞ አሁንም መቀጠሉ ተገለጸ።

በእስራኤል ሁከቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በጎዳና ላይ በመውጣት መንግስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ስልጣንን ለመንጠቅ ያወጣውን እቅድ ተቃውመዋል። እስራኤልን ያጨናነቁት እነዚህ ሰልፎች አሁን ላይ 11ኛ ሳምንቱን ይዟል። ይህ ግርግር እና ተቃውሞ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ መሆኑም ተነግሮለታል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ አዲስ አበባ

የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ህዝባዊ ተቃውሞው ኢኮኖሚውን ጎድቶታል፣ አልፎ ተርፎም አንዳንድ ተጠባባቂ የወታደራዊ ሃይሎች የጥሪ ትእዛዝን ላለመቀበል ዝተዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ፥ በፕሬዚዳንት ኢሳክ ሄርዞግ የቀረበውን የሽምግልና ሃሳብ ውድቅ በማድረግ አወዛጋቢ የሆነውን የለውጥ ፕሮግራም እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የሙስና ክስ እየቀረበባቸው ያሉት ኔታንያሁ ፥ ‘ከልክ በላይ የአክቲቪስቶችን ሥራ ነው የሚሰሩት’ ብለው የገለፁትን ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ለመግታት ማሻሻያው ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ ማሻሻያ ከተሳካ ፥ ለእሳቸው እና የእርሳቸው ቀኝ እጅ ለሆነው መንግስታቻው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔዎችን የመሻር እና ሁሉንም የዳኝነት ሹመቶች የመወሰን ስልጣን ይሰጣቸዋል ተብሏል።

አንዳንድ ተቺዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ግን ኔታንያሁ የጥቅም ግጭት እንዳለባቸው አጥብቀው ይገልጻሉ። ወደ ጎዳና የወጡትም በበኩላቸው ፥ የሚጠበቁት የኔታንያሁ እቅዶች የፍትህ ስርዓቱን እንደሚያደናቅፉ እና በህብረተሰቡ ውስጥ ክፍተቶችን እንደሚያሰፉ ይከራከራሉ።

 

 

20 March 2023, 13:19