ፈልግ

የዓለም የውሃ ቀን እ.አ.አ 2023 በየመን የዓለም የውሃ ቀን እ.አ.አ 2023 በየመን  (ANSA)

መንግስታት እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የውሃ ጉባኤ ላይ ዘላቂ ልማት ለማድረግ ቃል ገብተዋል!

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የዓለም የውሃ ቀን ስብሰባ የመጀመሪያ ቀን በዓለም ዙሪያ ከ 50 በላይ ታዋቂ ኩባንያዎች ዓለም አቀፍ የውሃ ቀውስን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ወደ ጉባኤው የተቀላቀሉ ሲሆን ፥ አሥር አዳዲስ አገሮች ደግሞ የተባበሩት መንግስታት የውሃ ስምምነትን ለመቀላቀል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ አዲስ አበባ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ኮንፈረንስ የመጀመሪያው ቀን የተጠናቀቀው በመንግስት እና በዋና ዋና ኩባንያዎች ስድስተኛውን ዘላቂ ልማት ግብ የሚደግፉ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ለማድረግ “ተደራሽ እና ዘላቂ የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ አስተዳደር” እንዲኖር ያለመውን ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነት ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ውሃ እና ማህበራት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግሎባል ኮምፓክት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለፀው ፥ ዓለም አቀፍ የውሃ ቀንን ለማክበር ከ50 በላይ የሚሆኑ ፥ ከ130 በላይ ሀገራት ውስጥ የሚሰሩ እና 2 ሚሊየን ሰዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በመቅጠር የሚያሰሩ ፥ የዓለም ታላላቅ ኮርፖሬሽኖች ፥ በውሃ ላይ የሚሰሩትን ተግባራት ለማፋጠን የቢዝነስ መሪዎቹ ግልፅ ጥሪ አድርገዋል። ጥሪውም ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የግሉ ዘርፉን እና የንግድ ማህበራትን በዉሃ ትግበራው ላይ የተባበረ እና ቁርጠኝነት የተሞላበት ትግበራ እንዲያሳዩ አካቷል። ይህም የጉባኤው ተቀዳሚ ውጤት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የተባበሩት መንግስታት ግሎባል ኮምፓክት ዋና ዳይሬክተር እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሳንዳ ኦጃምቦ እንዳወሱት “ኩባንያዎች በዓለም ትልቁ የውሃ ተጠቃሚዎች እንዴት እንደሆኑ አጉልተው ፥ የውሃ ሀብቶች በሃላፊነት ፣ በፍትሃዊነት እና በዘላቂነት እንዲተዳደሩ ሃላፊነት እንዳለባቸው አመላክተዋል። በማከልም "የግሉ ዘርፍ ጥሩ የውኃ ሀብት ጠባቂ እንዲሆን ማረጋገጥ አለብን" ብለዋል።

የውሃ ስምምነት

ሌላው አስደናቂ ስኬት ፥ በአፍሪካ ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በላቲን አሜሪካ የሚገኙ አስር ሀገራት ፥ የውሃ ኮንቬንሽን በመባል የሚታወቀውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስምምነትን ለመቀላቀል ያደረጉት ቁርጠኝነት ነው።

የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሃፊ ኦልጋ አልጋዬሮቫ የዚህን ሰነድ አስፈላጊነት ሲናገሩ “የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ትብብርን ለማስፈፀም ሁነኛ የሆነ ዓለም አቀፍ መሳሪያ ነው” ይላሉ። ‘እ.ኤ.አ. በ 1992 ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በጋራ ውሃ ላይ ከ 100 በላይ ስምምነቶች ተፈርመዋል’ ብለውም አክለውበታል ።

ውሃ እንደ የሕይወት ደም

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሁሉንም አባል ሀገራት የውሃ ኮንቬንሽኑን እንዲያከብሩ ጋብዘዋል ፤ ትብብርን በማሳደግ ፣ ግጭቶችን በመከላከል እና የመቋቋም አቅምን በመገንባት ረገድ ያላቸውን ጉልበት አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ጉተሬዝ ለጉባኤው በሰጡት አስተያየት ፥ ይህ የህይወታችን ደም ስር የሆነው እና ወሳኝ ሚና ያለውን ውሃችንን የሰው ልጅ ከልክ በላይ በሆነ ፍጆታ ዉሃን እንዴት እያደረቀው እንዳለ ፣ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ባልሆነ አጠቃቀም እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሙቀት መጨመር ምክንያት እንዴት በትነት እያለቀ እንደሆነ ደጋግመው በአጽንኦት ተናግረዋል።

ዋና ጸሃፊው አራት የተግባር ዘርፎችን ለይተዋል። እነዚህም የውሃ አስተዳደር ክፍተትን ማቀራረብ ፥ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ላሉ ሰዎች እኩል ተጠቃሚነት እንዲኖር ያስችላል ፣ በውሃ እና በንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶች ላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ፣ በመቋቋም ላይ ማተኮር፣ ይህም ማለት በአዳዲስ መሰረተ ልማቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማለት ሲሆን በመጨረሻም እጅግ አሳሳቢ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮችን መፍታት እንዳለብን ዘርዝረዋል።

ድንበር ተሻጋሪ ትብብር

ይህ የውሃ ስምምነት ተሳትፎ በጉባኤው ምልአተ ጉባኤ ወቅት በሃገራት መካከል የተደረገው የጋራ ጥረት ብቻ አልነበረም። የስሎቬኒያ ፕሬዝዳንት ናታሻ ፒሪክ ሙሳር ፥ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ትብብር ጥምረትን በመወከል እንዳስገነዘቡት ፥ በድንበር ተሻጋሪ ተፋሰሶች ላይ አዳዲስ እና ውጤታማ የሆኑ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩ እና በዓለም ዙሪያ ከ 3 ቢሊዮን በላይ ሰዎች ጥገኛ የሆኑበት ፥ ከዓለም 60 በመቶው የንፁህ ውሃ ፍሰትንም እንደሚሸፍን አስረድተዋል።

በድምሩ አርባ ግዛቶችን ያቀፈው ጥምረቱ ፥ ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን፣ የሰው እና የአካባቢ ጤናን፣ የብዝሃ ህይወትን፣ የአየር ንብረት ትግበራ እና የመቋቋም አቅም ማዳበርን፣ የአደጋ ስጋት ቅነሳን እና ሠላምን ለማስፈን በድንበር ተሻጋሪ መሬት ላይ መተባበር እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

ማስጠንቀቂያው "ውሃ ለትብብር" እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ በየደረጃው የሰላም አሽከርካሪ በመሆን ውሃን በተሻለ መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ላይ በማተኮር የዛሬውን ስብሰባዎች እና መስተጋብራዊ ውይይቶችን ጠብቋል።

 

24 March 2023, 10:48