ፈልግ

የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበት 60ኛ ዓመት መታሰቢያ የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበት 60ኛ ዓመት መታሰቢያ  (ANSA)

በውይይት እና በአንድነት ላይ የተመሠረተ የፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የውጭ ፖሊሲ ትሩፋት

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተገደሉበት 60ኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት፥ የውጭ ፖሊሲያቸውን ትሩፋት እና የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን በትክክል የመተርጎም አስፈላጊነት ላይ ያላቸውን ትምህርቶች እንቃኛለን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከጥር 12/1953 እስከ ህዳር 12/1956 ዓ. ም. ድረስ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከነበሩት ጆን ፍዝጌራልድ ኬኔዲ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ቢያንስ ሁለት ትምህርቶችን ማግኘት ይቻላል። የመጀመሪያው የስለላ አጠቃቀምን የሚመለከት ሲሆን፣ የምዕራባውያን የመከላከያ ሃይሎች በአሁኑ ጊዜ እየተጋፈጡ ያሉትን ግጭቶች ለመተንበይ አለመቻላቸው በሚነሳው ክርክር ወቅት ወቅታዊ ጠቀሜታ ያለው ርዕሠ ጉዳይ ነው። ለዚህም ጋዛ እና ዩክሬን ዋና ምሳሌዎች ናቸው። የጆን ኤፍ ኬኔዲ ተሞክሮ የውድቀት እና የስኬት ታሪክ ይነግረናል።

በአንድ በኩል እንደ ጎርጎሮሳዊው ሚያዝያ 15/1961 ዓ. ም. የተጀመረው የባሕር ወሽመጥ ወረራ ሲሆን፥ በግዞት የሚገኝ የኩባ አይሮፕላን በመምሰል የአሜሪካ አውሮፕላኖች የፈጸሙት የቦምብ ጥቃት ነበር። የዋሽንግተን ዓላማ የላቲን አሜሪካ አገር ኩባ የኮሚኒስት ቡድንን እንዳትቀላቀል መከላከል ነበር። የሲአይኤ እና የፔንታጎን ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ፥ የኩባ ገበሬዎች ፊደል ካስትሮን በጠላትነት ፈርጀው ስለ ነበር በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፉትን የኩባ ግዞተኞች ወረራን በመልካም ስሜት እንደሚቀበሉ ያምኑ ነበር። ይሁን እንጂ ክዋኔው ከተጀመረ ከሁለት ቀናት በኋላ ዓላማቸው ሳይሳካ ቀረ። ሕዝቡ ለኮሚኒስት አገዛዝ አጋርነቱን አሳየ። ምርኮኞቹ ታሰሩ፣ ይህም ፊደል ካስትሮ በዓለም ፊት ያላቸውን ተወዳጅነት አጠናከረ። ኬኔዲ በወቅቱ የሲአይኤ ኃላፊ የነበሩትን አለን ዱልስን በሌላ ሰው ቢተኩም ነገር ግን አሜሪካን ያጋጠመው ውድቀት በግልጽ የሚታይ ነበር።

ዴሞክራቱ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፥ እንደ ጎርጎሮሳዊው ጥቅምት ወር 1962 ዓ. ም. ለተከሰተው የሚሳኤል ቀውስ ጥንቃቄ በተሞላበት እና ተግባራዊ በሆነ አቀራረብ ታዋቂነትን ማግኘት ቻሉ። ጆን ኤፍ ኬኔዲ በአሥራ ሦስት ቀናት ውስጥ፥ በወቅቱ የሶቪዬት ፕሬዝደንት የነበሩት ኒኪታ ክሩሽቼቭ፥ በኩባ የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ሠፈር ለመገንባት ላሳዩት ተነሳሽነት ምን ዓይነት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው እና የኒውክሌር መስፋፋትን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ማሰብ ነበረባቸው። ለጥረቱ ስኬታማነት በዋናነት የተጠቀሰው በፕሬዝደንቱ እና በብሔራዊ የደኅንነት ጽሕፈት ቤት መካከል ያለው ቅንጅት ነበር። እንደ ጎርጎሮሳዊው ጥቅምት 16/1962 ዓ. ም. ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ሠፈር መገንባቱን በማስመልከት በ U2 አውሮፕላን ለተደረገው ጥናት ምስጋና ይግባውና የሶቪየትን እቅድ ተናግረው ነበር። መረጃው ከተገኘ በኋላ ሶቪዬት ኅብረት አሜሪካውያኑ ጣልቃ እንዲገቡ፣ እንዲደራደሩ ወይም ምን ያህል ለመጓዝ ፈቃደኞች መሆናቸውን እንዲገነዘቡ ማስገደድ ይፈልጉ ነበር። በመጨረሻ ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት መወሰን ነበረባቸው። በክሩሽቼቭ የተላለፈው ውሳኔ በሁለት ምክንያቶች ውጤታማ ሊሆን ችሏል። የመጀመሪያው፥ ጦርነትን ለማስጀመር የሶቪዬቶች ውሳኔ ምን እንደሆነ ማወቅ ሲሆን፥ ሁለተኛው የአሜሪካ መንግሥት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ባለመቻላቸው እና ርዕዮተ ዓለም ከስልት በልጦ እንዲያሸንፍ ፈቅደው ስለ ነበር ክሩሽቼቭ ስልት እንደሌላቸው ግልጽ ሆነ።

ከእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች የአንድ ሰው የማሰብ ችሎታ ምን ያህል እና አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት ይችላል። የውጭ ግንኙነት ዕውቀትን ለማሳደግ እና በዚህም በመታገዝ መረጃን ለመሰብሰብ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ መረጃን የማሰባሰብ፣ የማስተባበር፣ የመተርጎም፣ የመተንተን እና የመገምገሚያ ሂደት አለ። ይህም አንዳንድ ጊዜ ያልተለመዱ ተግባራትን ለምሳሌ መረጃን የማዛባት ወይም ጣልቃ ገብነትን ያካትታል። በእርግጠኝነት ሁሉም የስለላ ኤጀንሲዎች ውድቀት ያጋጥማቸዋል። በዚህ የተነሳ አንድ ሰው በሙያው ውድቀት ሊያጋጥመው እና አንዳንድ ጊዜም ፈታኝ የሆኑ መረጃዎችን እና ከውጭ ተዋንያን ጋር የተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ።

ሆኖም በዚህ አጠቃላይ ሂደት ውስጥ ከሌሎቹ ሁሉ የበለጠ ዋጋ ያለው እና ብዙ ጊዜ የሚሰማ አንድ ቃል አለ። ይህም የመረጃ አተረጓጎም የሚል ነው። የኢንተለጀንስ ኤጀንሲዎች ዛሬ ሊሰበስቡ የሚችሉት የመረጃ መጠን ከ1960ዎቹ እጅግ የላቀ ነው። ነገር ግን እነዚህን ሁሉ የመተርጎም አቅም እንዳለን እርግጠኞች ነን? ቴክኖሎጂ አስፈላጊ መሣሪያዎችን የሚያቀርብ ከሆነ የሰው አስተሳሰብ በእርግጥ ከዚህ ዓይነት ለውጥ ጋር አብሮ እንደሚሄድ ማረጋገጥ፣ የሥራ አቅጣጫን እና ስልትን መለየት፣ ባለሙያዎችን ማዳመጥ፣ መረጃን ማዋሃድ፣ ግልጽነት እና አርቆ አስተዋይነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እና በመረጃ ትንተና የተካኑ መሆናቸው ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ከሚሳኤል ቀውስ በኋላ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ነሐሴ ወር 1963 ዓ. ም. ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ እና ክሩሽቼቭ በዋይት ሃውስ እና በክሬምሊን መካከል ያለውን ቀጥተኛ ግንኙነት አጽድቀዋል። ውሳኔው በችግር ወቅት ምላሽ የሚሰጥበትን ጊዜ ለማሳጠር ብቻ ሳይሆን ይልቁን ከጠላት ጋር የመገናኘት አስፈላጊነትን፣ በሰላም አብሮ የመኖር ዘዴን እና የቀዝቃዛው ጦርነት መለያ የሆነውን በምሥራቁ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ያለው የጋራ ሕጋዊነት ሁኔታን መመልከት ነው። በጊዜ ሂደት በኃያላን መንግሥታት መካከል ያለውን አጠቃላይ ተቃውሞ ሳይመለከቱ ይልቁንም በየአካባቢያቸው ቁጥጥር ለማድረግ ያለመ መሆኑ ግልጽ ሆነ።

ይህ በዋናነት የሚያመለክተው፥ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በሐምሌ ወር 1961 ዓ. ም. ለብሔራዊ የደህንነት አማካሪያቸው ዋልት ሮስቶው በሰጡት መግለጫ፥ በምዕራባውያን ኃያላን ከሚተዳደረው ከምሥራቅ በርሊን ምዕራቡ ክፍል ከሰላሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ሲሰደዱ ክሩሽቼቭ ምሥራቅ ጀርመንን እንደሚያጡ ግልጽ ነበር። ይህ እንዲሆን መፍቀድ አይቻልም። ምክንያቱም ምሥራቅ ጀርመን በምዕራባውያን እጅ የምትወድቅ ከሆነ በፖላንድ እና በምስራቅ አውሮፓ ሁሉ ላይም ተመሳሳይ ነገር ይከሰታል። የስደተኞችን ፍሰት ለመግታት አንድ ነገር ማድረግ ይጠበቅ ነበር። ምናልባትም ግንብ መገንባት ይቻል ይሆናል። ነገር ግን የሕዝቡን ስደት በዚህ ማስቆም አይቻልም። የፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ አካሄድ አቅምን ማጣት ሳይሆን ስልታዊ ነበር። ሁልጊዜም ከጦርነት ትምህርት መቅሰም የተሻለ ነው።  እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ነሐሴ 13/1961 ዓ. ም. የበርሊን ግንብ ሲገነባ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፥ “ይህ ፍፁም መፍትሄ ባይሆንም ግንብ ከጦርነት እጅግ የከፋ ነው” ያሉበት ምክንያት ለዚህ ነበር።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በሰኔ 10/1963 ዓ. ም. ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ዋሽንግተን በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ባደረጉት ንግግር፥ ከሞስኮ ጋር የተደረሰው የኒውክሌር ሙከራ እገዳ ስምምነት ድርድር መጀመሩን ሲያስታውቁ፥ “ምን ዓይነት ሰላም እንፈልጋለን? በዓለም ላይ በአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች የሚመጣ ሰላም አይደለም። ነገር ግን ለአሜሪካ ሰላም ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ለሕዝቦች በሙሉ እውነተኛ ሰላም የሚገኝበትን እና ወደ ጥላቻ የሚወስዱ ግጭቶችን ማስወገድ የሚያስችል ስምምነት መሆን አለበት። ከውርደት የሚያተርፍ ወይም ካልሆነ ወደ ኒውክሌር ጦርነት የሚመራ ስምምነት መሆን አለበት።

ከፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ልምድ የምናገኘው ሁለተኛው ትምህርት የውይይት አስፈላጊነት ነው። ራስን መተቸት እና ለጠላት ያለውን አመለካከት እንደገና ማጤን፣ የመንግሥትን ውርደት እና የሕዝብን ጥላቻ ማስወገድ ነው። እነዚህ ጭብጦች ዛሬ ይበልጥ ጠቃሚ ናቸው፤ ምክንያቱም የዓለም አቀፉ ሥርዓት ከአሁን በኋላ ክፍፍልን እና ልዩነትን የሚደግፍ አይደለም። ዛሬ አልፎ አልፎ እየተካሄደ በሚገኝ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ እናገኛለን።

 

 

22 November 2023, 15:37