ፈልግ

በኪየቭ የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ካደረሰ በኋላ በኪየቭ የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ካደረሰ በኋላ 

የሩሲያ ጥቃት አይሎ የእህል አቅርቦት ላይ ስጋት እየፈጠረ ባለበት ወቅት ዩክሬን የረሃብ ቀን አከበረች

የዩክሬን መሪዎች እ.አ.አ. በ 1932-33 ድረስ ሆሎዶሞር በተባለው ረሃብ በርካታ ሚሊዮን ሰዎች የተጠቁትን ሟቾችን አስበው ውለዋል። ይህ 90ኛው ዓመቱን የያዘው በሀገሪቱ ከደረሱት ታይቶ ከማይታወቁት አስከፊ አደጋዎች አንዱ የሆነው የረሃብ አደጋ ታስቦ የዋለው፥ በሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ዩክሬን ውስጥ የሚገኘውን የእህል አቅርቦትን ለመጠበቅ አዲስ ስጋት ሆኖ በመጣበት ወቅት ነበር።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሕዝባቸው ጦርነት ላይ ባለበት እና የክረምቱ ወቅት እየገባ ባለበት ወቅት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ እና ባለቤታቸው ኦሌና አንዲት የድካም ስሜት የሚታይባት ወጣት ልጅ የስንዴ ዘለላዎችን ይዛ የሚያሳይ ሃውልት አጠገብ የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት አካሂደዋል።

የዩክሬን ባለስልጣናቱ የተሰበሰቡት በስታሊን ዘመን በተከሰተው ‘ሆሎዶሞር’ ተብሎ በሚጠራው እና አቻ ትርጉሙም ‘በረሃብ መሞት’ ማለት እንደሆነ የተነገረውን የረሃብ ጊዜያት 90ኛ ዓመት ለማስታወስ ነው።

እ.አ.አ. በ1932 ዩክሬን በሩሲያ የሚመራው የሶቪየት ህብረት አካል በነበረችበት ወቅት፥ የወቅቱ የሶቪየት ገዢ የነበረው ጆሴፍ ስታሊን ከዩክሬን እርሻዎች ላይ አዲስ የተሰበሰቡትን ሁሉንም እህል እና ከብቶች እንዲወረስ የሚል ፖሊሲ አወጣ። በዛን ወቅት ከተወረሱት ንብረቶች ውስጥ ቀጣዩን ሰብል ለመትከል የሚያስፈልገውን ዘርን ጨምሮ ነበር። በዚህ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዩክሬን ገበሬዎች በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ የታሪክ ተመራማሪዎች ‘በግልጽ የታቀደ የጅምላ ግድያ’ ብለው በገለጹት ረሃብ አለቁ።

ከ90 ዓመታት በኋላ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በሳምንቱ መጨረሻ የተፈፀመውን እና በርካታ ዩክሬናውያን የተጎዱባቸውን የሩሲያ በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃትን ከታሪክ ጋር በማገናኘት ማለትም የዩክሬን ገበሬዎች እህል እንዳይሰበስቡ እና እንዲሰደዱ በማድረግ ህዝቡን ለረሃብ ማጋለጥ እንደሆነ፥ ይህም የሆሎዶሞርን ታሪክ ሊደግም እንደሚችል ሞስኮን በተመሳሳይ ዘዴዎችን ከሰዋታል። ይሄም ጥቃት ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ከተፈፀሙት እጅግ የከፋው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ነውም ተብሏል።

እህል ከዩክሬን

ከሆሎዶሞር መታሰቢያ ጋር በትይዩ በተካሄደው “የእህል ከዩክሬን” ጉባኤ ላይ ፕረዚዳንት ዘለንስኪ ህዝቡ የዩክሬንን የምግብ አቅርቦት ከሩሲያ ጥቃቶች በተሻለ ሁኔታ እንዲከላከሉ አሳስበዋል፥ ምክንያቱም ደግሞ ይላሉ ዘለነስኪ ዩክሬን የዓለም የዳቦ ቅርጫት ናትና ብለዋል።

ባለፈው እህድ ዕለት በዩክሬን ያለው ምርት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ10 በመቶ ከፍ ያለ እንደሚሆን በመተንበዩ ተስፋ ተጥሎበታል። በዕለቱም ዩክሬን ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሩቡን ሰብል ብቻ እንደሚያስፈልጋት ተናግራለች።

ለዚህም ነው ‘እህልን ከዩክሬን’ በተባለው ጉባኤ ላይ እህል በጣም ለሚያስፈልጋቸው ሀገራት የዩክሬን እህል ለመግዛት ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር የተሰበሰበው። ጣሊያን እና ሊቱዌኒያ ለሰብአዊ ምግብ ፕሮግራም 4 ሚሊዮን ዩሮ በማዋጣት ከዋና ዋና እርዳታ ሰጪዎች መካከል ናቸው።
 

28 November 2023, 06:59