ፈልግ

ከህዳር 19 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ “ኢኮኖሚውን እንደገና ማስጀመር” በሚል ጭብጥ በካስቴል ጋንዶልፎ መንደር ዓለም አቀፍ ስብሰባ ይደረጋል ከህዳር 19 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ “ኢኮኖሚውን እንደገና ማስጀመር” በሚል ጭብጥ በካስቴል ጋንዶልፎ መንደር ዓለም አቀፍ ስብሰባ ይደረጋል   (Copyright (c) 2020 j.chizhe/Shutterstock. No use without permission.)

ገደብ የሌለነበት ኢኮኖሚ ወደ ተሃድሶ የሚደረጉ መንገዶች ይገድባል ተባለ

ከህዳር 19 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ “ኢኮኖሚውን እንደገና ማስጀመር” በሚል ጭብጥ በካስቴል ጋንዶልፎ መንደር ዓለም አቀፍ ስብሰባ እንደሚካሄድ የታወቀ ሲሆን፥ በ “ፍራንችስኮስ ኢኮኖሚ” አስተባባሪነት የሚዘጋጀው ይህ ዓለም አቀፍ ስብሰባ፥ ኢኮኖሚን በኢዮቤልዩ አንፃር እንደገና ለማጤን፣ በማህበራዊ ፍትህ፣ በምድራችን እንክብካቤ እና ከዕዳ ነፃ መሆን ላይ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ከታሪካችን የመጀመሪያ ጊዜያት ጀምሮ የሰው ልጅ ፈጠራ እና ብልሃት ገደቦችን እንድናሸንፍ እና አዳዲስ እውነታዎችን እንድንፈጥር እና እንድንቀርጽ አስችሎናል።

ለዚህም በቴክኒክና በቴክኖሎጂ በተደረጉት ግስጋሴዎች ላይ አሁን ያለንበት ዓለም ምስክር ነው። ገደቦችን ማሸነፍ የማንነታችን አካል ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ረዳት ፈጣሪዎች መሆን የኛ ጥልቅ ፍላጎት ነው። እድሎችን እንፈልጋለን፣ እራሳችንን ለመግለጽ እንናፍቃለን። ገደቦችን ማሸነፍ ሁል ጊዜ አዳዲስ እውነታዎችን እንድናውቅ እና እንድንገልጥ ያደርገናል፥ ነገር ግን በሥነ-ምህዳር ማለትም በምድር ላይ፣ በሕያዋን ፍጥረታት እና በሰው ልጅ ሕይወት መዛባት እየታወቀ ባለው ዓለም ውስጥ ገደቦች አሁን ባለንበት ጊዜ እንደገና ሊደረስበት የሚገባውን ትርጉም እና ጉልበት ይይዛሉ።

ብዙውን ጊዜ ነፃነታችንን የሚገድብ ከሚመስለው አሉታዊ ነገር ጋር የተያያዘው ገደብ እድሎችን የሚሰርዝ ሳይሆን አዳዲስ እድሎችን ይከፍታል። ‘ሊምስ’ ከሚለው የላቲን ቃል የመጣው ‘ሊሚት’ ወይም በአማርኛው ገደብ፥ ወሰን፣ ድንበር፣ ጠርዝ ወይም የመለያ መስመርን የሚያመላክት ሲሆን፥ - በሮማ ግዛት ውስጥ ግድግዳ ሳይሆን ድንበርን የሚያመላክት መንገድ እንደነበር እና አንድ ነገር የሚጀምርበት እና የሚያልቅበትን ቦታ ለመጠቆም በምድሪቱ ላይ የሚቀመጥ ምልክት ማለት ነው።

ገደቦች አስፈላጊ የሆኑ የበቂነት፣ ተቀባይነት እና የአቀባበል ስሜትን የሚሰጡ ሲሆን፥ ከገደቡ በፊት ከእኛ አቅም የሚሻገሩ ነገሮች ላይ ለማሰላሰል እና ራሳችን ለጥቃት የተጋለጥን መሆናችንን በመገንዘብ ምን ያህል እንደሚበልጠን ማወቅ እንችላለን። ስለዚህ እውነታውን እንደሁኔታው በመገንዘብ አማራጮችን በመውሰድ ፈጠራን ማንሳት እና አዲስ ነገር ሊፈጠር ይችላል። ሆኖም ማህበረሰቦቻችን ገደቦችን በማሸነፍ ብቻ ሳይሆን በማጥፋት የተጠመዱ ይመስላሉ።

መቼም ቢሆን ምንም በቂ ነገር አይኖርም፥ እድገት፣ ፍጥነት፣ ቁሳዊ እና ዲጂታል ፍጆታ፣ የሥራ ሰዓት, ወዘተ በቂ አይደሉም። ብዙ ባወቅን ቁጥር የምናውቀው ነገር ትንሽ መሆኑን እንረዳለን፥ ሆኖም አሁንም ድረስ ገደቦችን ለመቀበል እንቸገራለን። 

ሳይንስ እና ቴክኒክ ሞትንም ጨምሮ ሁሉንም የሕይወታችን ገጽታ ሊፈታ እንደሚችል እንዲሁም የሕይወት እና የትርጉም ምንጭ ናቸው የሚለውን ቅዠት ፈጠርን። ይህ በእርግጥ ነፃነታችንን እና የሰው ልጅ እድገታችንን ይገድባል።

የዘንድሮው የኢዮቤልዩ በዓል አንድ ነገር የሚጀመርበት እና የሚያልቅበትን ቦታ ለመጠቆም በምድሪቱ ላይ የተገኘ ዱካ ነው። ገደብን ወይንም ወሰንን የሚያመላክት መስመር ሲሆን በጊዜ እና በቦታ ውስጥ ለነጻነት፣ ለተሃድሶ እና ለማረፍ እድልን ይከፍታል። ከዚህ በኋላ መቀጠል የማይገባውን እንድናቆም የሚገፋፋን አንዱ መንገድ ሲሆን፥ ኢፍትሃዊነት፣ ድህነት፣ ጦርነት፣ የሀብት መሟጠጥ እና የእኛ ያልሆነው እረፍት የለሽ ዲጂታል ጉዞ እንዲሁም የሰውን ልጅ ክብር እና ምድርን የሚጎዳ ያልተጣራ ክምችት እንድናቆም ያበረታታናል።

ይህ ኢዮቤልዩ አስፈላጊ የሆነውን እና በቂ የሆነ ኢኮኖሚን የሚፈታተነውን ነገር በማወቅ እንደ አንድ የነፃነት መንገድ የገደቦችን ዋጋ እንደገና እንድናገኝ የተደረገልን ግብዣ ሲሆን፥ የጋራ ጥቅምን በማዕከሉ ላይ የሚያኖር፣ ተስፋን የሚፈጥር እና ከመዝጋት ይልቅ አድማስን የሚከፍት ነው።

ለሁሉም ህይወት ያላቸው ፍጥረታት ፍትህን ለመጠበቅ የተዘጋጁ እነዚህ ገደቦች የተቀመጡበት ኢኮኖሚ፥ እድገትን ወይም ሃብትን በተለየ መንገድ እንድንመለከት የተደረገልን ግብዣ ወይም ክምችትን፣ ስልጣንን ወይም ኢፍትሃዊነትን የምንገድብበት አይደለም። ገደቦች በቀላሉ ቴክኒካል ወይም ቁሳዊ ሳይሆኑ ከሁሉም በላይ ሰብዓዊ እና መንፈሳዊ ናቸው። ሁሉንም ግንኙነታችንን እንደገና እንድናጤነው የተደረገልን ጥሪ ነው።

በዚህ ምቹ የኢዮቤልዩ ዓመት ኢኮኖሚውን እንደገና ለማስጀመር ስንፈልግ፣ ከገደብ አንፃር መቅረብ ማለት ከእግዚአብሔር እና ከምድር ጋር ያለንን ግንኙነት ማስማማት ማለት ነው። እኛ ውስን ፍጥረታት ነን፥ በጣም የተወደድን፥ ነገር ግን ውስን ነን።

ምድራችን ፍሬያማ ሆነን ፍሬ ለማፍራት እንድንችል ከእግዚአብሔር የተሰጠን ልዩ ስጦታ እንጂ እኛ ዓለምን አልፈጠርንም።

እኛ የበላይ እንደሆንን አድርገን ማየቱን ከቀጠልን ሰዎችን ጨምሮ ያለማቋረጥ መጠቀማችንን እንቀጥላለን፥ የምንኖርበት የመኖሪያ ቤት መሆኑን እንደ ገና ልናገኘው ያስፈልገናል።

ከዚህ ልምድ በመነሳት እና እራሳችንን ድንበሮቻችንን በሚገባ እንደሚያውቅ አንድ ሰው ትክክለኛ ቦታ ላይ በማስቀመጥ የኃላፊነት እና የመተሳሰብ አመለካከትን ከስር መሰረቱ መጣል ይቻላል። ከዚህ መሰረት በመነሳት እርስ በርስ እና ከራሳችን ጋር የተሻለ ግንኙነት መፍጠር ይቻላል።

በቂ የሆነ ኢኮኖሚ እኛም ሆንን ማንም ሰው በማንነታችን እንጂ በቁሳቁስ እንዳልተገለፀ በመረዳት የበለጠ የምንጋራበት ቀለል ያለ የአኗኗር ዘይቤ መግቢያ በር ሊሆን ይችላል። በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ መኖር ወይም ደስተኛ አለመሆን ሳይሆን ነገሮች መቼም አይበቁም ከሚል ሃሳብ እራሳችንን በማላቀቅ በምስጋና ስለማረፍ እና አንዳችን ለሌላው ጠባቂ መሆን ነው። ለትክክለኛው ጉዳይ ጊዜ እና ቦታ መፍጠር ነው። ለምሳሌ ማቀፍ ፍቅርን እንድንለማመድ የሚፈቅድ ገደብ ነው!

ኢዮቤልዩ ሁል ጊዜ የማይቻለውን እና አንዳንድ ጊዜ የማይቻል የሚመስለውን ይቅርታን፣ መልቀቅን… ይጠይቃል፥ ግን ይህ ብዙ ጊዜ የሚቻል ቢሆንስ? ኢኮኖሚያችን በእውነት እንደገና ቢጀምር እና የትግል፣ የማይረካ ፍላጎት፣ የድካም ቦታ ሳይሆን፥ ነገር ግን ማበብን፣ ማረፍን፣ ውበትን ማሰላሰልን እና ግንኙነቶችን የሚያበረታታ ገደብ ያለው ቦታ ሊሆን ቢችልስ?

ይህ ምቹ የሆነው የኢዩቤሊዩ ዓመት ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት የራሳችን፣ የምድራችን እና የኢኮኖሚ ገደቦችን እንደገና የማግኘት ግብዣ በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት የሚያልቅ ሳይሆን፥ ይልቁንም እየጠነከረ ይሄዳል። ዛሬ ሕይወታችን ምን ዓይነት ገደቦች ያስፈልጉታል?

ይሄንን በትክክል ለይቶ ማወቅ ያስፈጋል።

24 Nov 2025, 15:50