ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የክርስቲያን ምስክርነት መንፈሳዊ የልብ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋል አሉ!

የጎርጎስሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ-ክርክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የገና በዓል በታኅሳስ 15/2016 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከተከበረበት የገና በዓል በመቀጠል ባለው እለት የቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ሰማዕት ተብሎ የሚጠራው የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል እንደ ሚከበር ይታወቃል። ይህ በዓል በታኅሳስ 16/2016 ዓ.ም በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን ባደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ገለጹት የክርስቲያን ምስክርነት መንፈሳዊ የልብ ለውጥ እንዲመጣ እና በሕይወታችን ውስጥ የእምነት ተአምራት እንዲፈጠር ይመራል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰንድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የገናን በዓል ካከበርን ከአንድ ቀን በኋላ የቀዳማዊ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስን በዓል እናከብራለን። የሰማዕትነቱን ታሪክ በሐዋርያት ሥራ (ምዕራፍ 6-7) ውስጥ እናገኘዋለን፣ እሱም እርሱን መልካም ስም ያለው፣ ለድሆች ምግብ ያቀርብ የነበረ እና የበጎ አድራጎት ተግባር ስያከናውን የነበረ (የሐ. ሥራ 6፡3) ሰው አድርጎ ያቀርበዋ። በትክክል ለዚህ ለጋስ ታማኝነት፣ ለእርሱ በጣም ውድ የሆነውን ነገር ማለትም በኢየሱስ ላይ ያለውን እምነት ከመመስከር በቀር ሌላ ጥፋት ያልፈጸመ ሰው ሲሆን ይህም መልካም ተግባሩ የጠላቶቹን ቁጣ አስነስቷል፣ እነሱም ያለርህራሄ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል። ይህ ሁሉ የሆነው ለግድያው “ዋስትና” ሆኖ በሚያገለግለው ወጣቱ ሳውል፣ የክርስቲያኖችን ቀናተኛ አሳዳጅ በሆነው ሰው ፊት ነው (የሐ. ሥራ 7፡58)።

እስቲ ይህን ትዕይንት ትንሽ እናስብ፡- ሳኦልና እስጢፋኖስ፣ አሳዳጁና ተሳዳጁ። እንደ ወጣቱ ፈሪሳዊ መሠረታዊነት እና ሞት የተፈረደበት ሰው ላይ የተወረወረው ድንጋይ ያህል በመካከላቸው የማይገሰስ ግድግዳ ያለ ይመስላል። ነገር ግን ከመታየት ባለፈ፣ አንድ የሚያደርጋቸው የበለጠ ጠንካራ ነገር አለ፡ በእስጢፋኖስ ምስክርነት፣ ጌታ እርሱ ሳውቅ በሳኦል ልብ አስቀድሞ መልካም ነገሮችን እያዘጋጀ ነው፣ ታላቁ ሐዋርያ ጳውሎስ እንዲሆን የሚያደርገውን የልብ መለወጥ። እስጢፋኖስ አገልግሎቱ፣ ጸሎቱ እና የሚያውጀው እምነት፣ በተለይም በሞት ጊዜ ይቅርታ ማድረጉ ከንቱ አይደለም። በምንም የማያልቁ ይመስላሉ ነገር ግን በተጨባጭ የሱ መስዋዕትነት ወደ ድንጋዮቹ በተቃራኒ አቅጣጫ በመሄድ እራሱን በድብቅ መንገድ በመትከል በከፋ ተቀናቃኙ እቅፍ ውስጥ በመትከል ፣የድንጋይ ልቡን ወደ ሥጋ ልብ እንዲለውጥ የሚያደርግ ዘር ይተክላል (ዕዝ. 36፡26)። ምናልባት ጳውሎስ ከአመታት በኋላ “እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ፣ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ እንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን አሳድጃለሁ (1ቆሮ. 15፡9-10) ብሎ ሲጽፍ ይህን ጊዜ ያስብ ይሆናል።

ዛሬ ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ስደቱ እንደቀጠለ እናያለን፡ አሁንም አሉ - ብዙዎችም አሉ - ስለ ኢየሱስ ለመመስከር የሚሰቃዩ እና የሚሞቱ፣ በተለያዩ ደረጃዎች የሚቀጡ እንዳሉ ሁሉ ከወንጌል ጋር በሚስማማ መንገድ መስራታቸውን እና በአለም ሲሳለቁ እና ሲሰብኩ ለመልካም ተግባራቸው ታማኝ ለመሆን በየቀኑ የሚጥሩ ሰዎች አሉ። እነዚህ ወንድሞችና እህቶችም የከሸፉ ሊመስሉ ይችላሉ፤ ዛሬ ግን እንደዚያ እንዳልሆነ እናያለን። አሁን እንደዚያውም፣ የመሥዋዕታቸው ዘር፣ የሚሞት የሚመስለው፣ ያበቅላል፣ ፍሬም ያፈራል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእነሱ በኩል ተአምራትን በማድረግ ይቀጥላል፣ (ሐዋ. 18፡9-10)፣ ልብን በመቀየር ሰዎችን ማዳን ይቀጥላል።

እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ፡- በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ዛሬም ለእምነት ሲሉ ለሚሰቃዩትና ለሚሞቱት እጨነቃለሁ እና እጸልያለሁ ወይ? እናም በተራው፣ በየዋህነት እና በመተማመን ወንጌልን ያለማቋረጥ ለመመስከር እሞክራለሁ ወይ? ፈጣን ውጤት ባላገኝም የመልካምነት ዘር ፍሬ ያፈራል ብዬ አምናለሁ ወይ?

ስለ ኢየሱስ እንድንመሰክር የሰማዕታት ንግሥት የሆነችው እርሷ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

27 December 2023, 10:41

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >