ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 'የእስያ ልብ ወደ ሆችው ሀገር ሄጄ ነበር እናም ለእኔ ጥሩ ነገር ተስምቶኝ ነበር ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየሳምንቱ ረቡዕ እለት በሚያካሂዱት የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ በቅርቡ ወደ ሞንጎሊያ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ በተመለከተ ቅዱስነታቸው መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን 'የኢስያ ልብ በሆነችው ሀገር ውስጥ ቆይታ አድርጌ ነበር እናም ለእኔ መልካም ነገር አድርጎኛል' በማለት ተናግሯል፣ እናም እግዚአብሔርን የሚወዱ እና የሚሹ ሰዎችን እርሱ 'የዋህ ልቦችን' እንዴት እንደሚፈልግ ጠቁመዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"የእስያ ልብ ወደ ሆነችው ሀገር ሄጄ ጥሩ ነገር ተደርጎልኛል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ በሞንጎሊያ ያደረጉትን 43ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ በእለቱ ጳጉሜ 01/2015 ዓ.ም እርሳቸው ዘወትር ረቡዕ እለት የሚያደርጉትን የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው ተናግረው ነበር።

ቅዱስ አባታችን የቻይና እና የሩሲያ አዋሳኝ የሆነችውን የእስያ ሀገር ጎብኝተው ነበር፤ በጠቅላላው ወደ 1,500 የሚጠጉትን የሞንጎሊያ ካቶሊካዊ ማኅበረሰብ ያላቸውን ቅርበት ለመግለጽ እና ለማበረታታት ነበር ቅዱስነታቸው ወደ እዚያው ያቀኑት።

በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝታቸውን በጸሎታቸው ላጀቡ ምዕመናን ሁሉ ምስጋናቸውን ገልፀው እርሳቸውን በሞንጎሊያ ለመቀበል ከፍተኛ ዝግጅት ያደርጉትን ሰዎች በሙሉ ከልብ አመስግነው በተለይም “የተከበሩ እና ብልህ” የሆኑትን የሞንጎሊያ ሕዝብ “እንዲህ ያለውን ፍቅርና አክብሮ” ስላሳዩ ምስጋናቸውን በድጋሚ አቅርበዋል።

ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን የጀመሩት አንዳንዶች “ለምን ጳጳሱ ጥቂት አማኞችን ለመጎብኘት ርቀው ይሄዳሉ?” ብለው ሊጠይቁ እንደሚችሉ በማመን ነው። እርሳቸውም ለእዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ “በትክክል እንደዚያ ስለሆነ፣ ከድምቀት ርቀው ስለሚገኙ፣ ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔር መገኘት ምልክቶችን በእዚያ ስለምናገኝ፣ እግዚአብሔር ልብን እንጂ መልክን ስለማይመለከት ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጌታ የዋህ ልቦችን ይፈልጋል

"ጌታ ማዕከላዊ መድረክን አይፈልግም" በማለት ቅዱስ አባታችን አጉልተው ገልጸዋል ይልቁንም "ሳይገለጡ እርሱን የሚፈልጉ እና የሚወዱትን የዋህ ልብ ከሌሎች በላይ ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ የማይፈልጉ" ሰዎችን ጌታ ይወዳል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሞንጎሊያ ባዩት ታላቅ ጸጋ ተደስተዋል፣ “ትሑት እና ደስተኛ ቤተክርስቲያን”፣ “በእግዚአብሔር ልብ” ለመገናኘት፣ “በጥቂቶች የቤተክርስቲያን አባላት መሃል በመገኘታቸው ደስታዬን መመስከር እችላለሁ” ብሏል ቅዱስነታቸው።

ቅዱስነታቸው ትኩረታቸውን ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ባዞሩበት ወቅት “አስደሳች ታሪክ” ተናግሯል።

"የእግዚአብሔር ቸርነት ከሐዋርያዊ ቅንዓት ተነስቷል - በዚህ ጊዜ እያሰላሰልንበት የምንገኘው ጉዳይ የአንዳንድ ሚስዮናውያን ወንጌልን ለመስበክ የነበራቸው ፍቅር ለመግለጽ ከሠላሳ ዓመት በፊት ወደዚያ ወደማያውቁት ሀገር ሄደው ነበር ። የሀገሪቷን ቋንቋ የማይችሉ እና ምንም እንኳን ከተለያዩ አገራት የመጡ ቢሆኑም "አንድ እና እውነተኛ የካቶሊክ ማህበረሰብን ፈጥረዋል" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግሯል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማህበረሰቡን የካቶሊካዊነት ተምሳሌት በማለት አወድሰውታል፣ እሱም “በሥጋ የተገለጠ ዓለም አቀፋዊነት፣ በሚኖርበት ቦታ መልካሙን የሚይዝ እና አብሮት የሚኖረውን ሕዝብ የሚያገለግል” በማለት ገልጿል።

የኢየሱስን ፍቅር በየዋህነት መመስከር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የኢየሱስን ፍቅር በየዋህነት፣ ከቃላት በፊት ባለው ሕይወት፣ በእውነተኛ ሀብቷ ደስተኛ በመሆን፣ ጌታን፣ የወንድሞቿን እና እህቶቿን አገልግሎት በመመስከር ቤተክርስቲያን እንደዚህ ትኖራለች" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያቺ ወጣት ቤተክርስቲያን የተወለደችው በበጎ አድራጎት ሥራ እንቅስቃሴ ነው ሲሉ የገለጹ ሲሆን ይህም የእምነት ምርጥ ምስክርነት ነው ብሏል፣ በማከልም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ‘የምሕረት ቤት’ የተሰኘውን የበጎ አድርጎት መስጫ ተቋም በመባረክና በመመረቅ ያጋጠማቸውን ደስታ አስታውሰዋል።

ያ ቤት “እያንዳንዱ ማህበረሰባችን የምሕረት ቤት እንዲሆን፡ ክፍትና እንግዳ ተቀባይ፣ የእያንዳንዱ ሰው ሰቆቃ ያለ ኀፍረት የሚገባበትና ከሚፈውሰው የእግዚአብሔር ምሕረት ጋር የሚገናኝበት” ቦታ ይሆን ዘንድ ጥሪ አቀረባለሁ ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሞንጎሊያን ሚስዮናውያን ቤተክርስቲያን አወድሰዋል፣ እናም እሁድ ነሐሴ 28/2015 ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በኡላንባታር አድርገውት የነበረውን ስብሰባ አስታውሰዋል። የሞንጎሊያ ትርጉም ያለው ጉብኝት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ወደ እስያ አህጉር ልብ ወደ ሆነችው አገር ሄጄ ጥሩ ነገር ገጥሞኛል" ብለዋል። "ሥር መሰረቶቻቸውን እና ባህላቸውን የሚንከባከቡ፣ ሽማግሌዎቻቸውን የሚያከብሩ እና ከአካባቢው ጋር ተስማምተው የሚኖሩትን የሞንጎሊያ ሰዎች ማግኘቴ ጥሩ ነበር፡ ወደ ሰማይ የሚመለከቱ እና የፍጥረት እስትንፋስ የሚሰማቸው ህዝቦች ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሞንጎሊያን “ወሰን የለሽ እና ጸጥታ የሰፈነባት አገር” በማስታወስ “የዓይናችንን ወሰን ለማስፋት፣ የሌሎችን መልካም ነገር ለማየት እና የአስተሳሰብ አድማሳችንን ለማስፋት እንድንችል” አብረው እንዲሰሩ ምእመናን አሳስበዋል።

Photogallery

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጳጉሜ ዓ.ም ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የሚያሳዩ ምስሎች
06 September 2023, 14:06

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >