ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የቅድስት ጆሴፊን ባኪታ ሕይወት የእግዚአብሔርን ጸጋ ይገልጣል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በመስከረም 30/2016 ዓ.ም ባደርጉት አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም ሐዋርያዊ ቅንዓት በሚል አርእስት ጀምረውት ከነበረው የጠቅላላ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ሕይወትን የመለወጥ ኃይል የገለጸላትን ቅድስት ጆሴፊን ባኪታ ሕይወት የተመለከተ እንደ ነበረ ተገልጿል፣ የቅድስት ጆሴፊን ባኪታ ሕይወት የእግዚአብሔርን ጸጋ ይገልጣል ማለታቸው ተገልጿል፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው በሱዳን ሰላም እንዲሰፈን ምዕመናን ጸሎት ማድረግ ይኖርባቸዋል ብሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ‹‹ቅድስት ጆሴፊን ባኪታ፣ በእርሷ አርአያ፣ በመጨረሻ ከባርነት እና ከፍርሃታችን ነፃ የምንወጣበትን መንገድ ያሳየናል፣ “ግብዝነታችንን እና ራስ ወዳድነታችንን የምንገልጥበት፣ ቂምን እና ግጭቶችን የምናሸንፍበት” ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት መንገድ ያሳየናል ማለታቸው ተገልጿል። ለእራሳችን፣ በቤተሰባችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ ሰላም እናገኛለን፣ እናም "በእነዚህ አስቸጋሪ በሆኑ አለመተማመን እና በሌሎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነን የተስፋ ብርሃን ይሰጠናል ሲሉ አክለው ገልጿል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ማሳሰቢያ ያቀረቡት ረቡዕ እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ሱዳናዊ በነበረቺው በቅድስት ጆሴፊን ባኪታ ሕይወት ዙሪያ ላይ ባደረጉት አስተምህሮ ላይ ነበር ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሐዋርያዊ ቅንዓት ባሳዩ ግለሰቦች ሕይወት ዙሪያ ላይ ያቀረቡትን ተከታታይ ትምህርት በመቀጠል፣ እንደገና ወደ አፍሪካ አህጉር ዘወር ብለዋል።

"ለሱዳን ህዝብ እንጸልይ"

ቅዱስ አባታችን ቅድስት ባኪታ ከሱዳን የመጣችበትን አመጣጥ በማስታወስ ነበር አስተምህሯቸውን የጀመሩ።

"በሚያሳዝን ሁኔታ ሱዳን ለወራት እየፈራረሰች ትገኛላች፣ ዛሬ ብዙም ባልተባለበት እና ብዙ ባልተዘገበበት አስከፊ የትጥቅ ግጭት፣ የሱዳን ህዝብ በሰላም እንዲኖር እንፀልይ!" ብሏል።

“በሚያሳዝን ሁኔታ ሱዳን ለወራት ያህል ዛሬ ብዙም ያልተነገረለት በአስከፊ የትጥቅ ግጭት ፈራርሳለች። ለሱዳን ሰዎች በሰላም እንዲኖሩ እንጸልይ! ብሏል።

ምእመናን በቅድስት ባኪታና በምስክርነቷ “ኃይለኛ ምስክርነት” መነሳሳት እንዳለባቸው በማሳሰብ ይህ መከራ ቢደርስባቸውም የቅድስት ባኪታ ዝናም ድንበር ተሻግሮ ማንነቱንና ክብር ለተነፈጉ ሁሉ መድረሱን ብፁዕ አባታችን አበክረው ተናግረዋል።

የማይነገር መከራ ቢኖርም ተስፋ አትቁረጡ።

በሱዳን ዳርፉር የተወለደችው ቅድስት ባኪታ በልጅነቷ ታፍና ለባርነት ተሽጣ እንደነበር አስታውሰዋል። ግፍና መከራ የደረሰባት ቢሆንም፣ ተስፋ አልቆረጠችም በማለት አስታውሰዋል።

ቅዱስ አባታችን ይህ በቅድስት ባኪታ ላይ የደረሰው መስቀል የሚመስል ስቃይ እንዴት ሕይወቷን እንደ ደገፋት አስታውሰው፣ አንድ ቀን አሳዳጊዋ ትንሽ መስቀል እንደሰጣት፣ እሷም ከእዚህ ቀደም የእዚህ ዓይነት ነገር ምንም አይታ የማታውቅ ቢሆንም ነገር ግን ይህንን ትንሼዬ መስቀል እንደ አንድ ትልቅ “ሀብት” አድርጋ ጠብቃው አቆየችው ብሏል። 

በክርስቶስ መስቀል ውስጥ፣ ቅዱስ አባታችን እንደገለፁት፣ የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን ያለንን የተፈጥሮ ክብራችንን የሚያረጋግጥልን፣ “እውነተኛ ነፃነትን” የሚያመጣ እና “የሚበደሉንን ይቅር እንድንል እና በእውነት እንድንወድ” የሚያስችለንን የምህረት ፍቅር ምንጭ እንዳገኘች ተናግራለች ብሏል።

ራሷን ለክርስቶስ ሰጠች።

የእግዚአብሔር ምህረት እና የይቅርታ ልምድ፣ ጳጳሱ አጽንኦት ሰጥተው እንደ ተናገሩት ከሆነ ቅድስት ባኪታ እንደ ሀይማኖተኛ እራሷን ለክርስቶስ እንድትሰጥ እና ሌሎችን በትህትና እና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ  አዲስ የመኖሪያ ስፍራዋ በሆነ በጣሊያን እንድታገለግል አነሳስቷታል ብለዋል።

የቅድስት ጆሴፊን ባኪታ ሕይወት “የእግዚአብሔርን ጸጋ ሕይወትን የመለወጥ ኃይልን ያሳያል፣” “ግጭቶችን ለመፍታት” እና “በእኛ ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ፍትህ፣ እርቅ እና ሰላምን ያመጣል” በማለት አስታውሰዋል።

የይቅርታ እና የሰላም ፍላጎት

"ውድ ወንድሞች እና እህቶች ይቅር ማለት ለይቅር ባዩ ሰው ክብርን ይጨምርለታል፣ እንጂ ምንም አይወስድበትም። ከራሳችን ወደ ሌሎች እንድንመለከት ያደርገናል ልክ እንደ እኛ ደካማ እንደሆኑ አድርገን ለማየት፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ወንድሞች እና እህቶች የጌታ ልጆች ነን” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግሯል።

“ይቅር ማለት እንደ ቅድስት ባኪታ ትሑት እና ደስተኛ የሆነ ቅድስና የሚጠራ ምሕረት የሚሆን የቅንዓት ምንጭ ነው” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አስተምህሮዋቸውን አጠናቋል።  

12 October 2023, 15:39

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >